
Ethiopia Check
59 subscribers
About Ethiopia Check
ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል።
Similar Channels
Swipe to see more
Posts

#FakeNewsAlert ፖፕ ፍራንሲስ ህይወታቸው እንዳለፈ ብሄራዊ ቴሌቭዥኑን ጨምሮ በአንዳንድ ሚድያዎች የተላለፈው ሀሰተኛ መረጃ እንዴት ተከሰተ? "የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል" በማለት የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ከጥቂት ሰአታት በፊት ያሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነበር። ጣብያው ለምንጭነት የአለም አቀፉን የዜና ወኪል አሶሲየትድ ፕረስ (AP) በምንጭነት ዋቢ ቢያደርግም "Pope Francis rested during a peaceful night following respiratory crisis" ከሚለው አርዕስት ውስጥ 'rested' ወይም 'እረፍት አደረጉ' የሚለውን 'ህይወታቸው አለፈ' የሚል ትርጓሜ ሰጥቶት እንደነበር ኢትዮጵያ ቼክ ያደረገው ዳሰሳ እና ማጣራት ያሳያል። በተመሳሳይ ድሬ ትዩብ የኢቢሲን ዘገባ ሳይጠቅስ ሊቀ ጳጳሱ እንዳረፉ አለም "አቀፍ ሚድያዎች እየዘገቡት ይገኛሉ" በማለት የተሳሳተ መረጃ አቅርቦ ነበር። አሁን ላይ ሁለቱም ሚድያዎች ዜናዎቻቸውን አንስተዋል። ኢቢቢ በሊቃነ ጳጳሱ ዙርያ የተሳሳተ ዜና ሰርቷል በማለት የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ያስታወቀች ሲሆን "እንደውም ዛሬ ከበፊት ቀናት በተሻለ ሁኔታ ሰላማዊ እንቅልፍ ተኝተው ነው ያደሩት" በማለት ገልፃለች። ፖፕ ፍራንሲስ የመተንፈሻ አካላቸው ላይ ጠንካራ ህመም ተከስቶባቸው ሆስፒታል ገብተው እንደሚገኙ አለም አቀፍ ሚድያዎች እየዘገቡ ይገኛሉ። ሚድያዎች ሰበር ዜናዎችን ለማጋራት በሚጣደፉበት ግዜ እንዲህ አይነት የትርጉም እና የይዘት ግድፈት ሊያጋጥማቸው ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው ኢትዮጵያ ቼክ ለማሳሰብ ይወዳል። ኢትዮጵያ ቼክ!

#FactCheck 'ብሔራዊ ባንክ ለመንግሥት አበድሮ ያልመለሰለት ገንዘብ 92.1 ቢሊዮን ብር ደረሰ' በሚል እየተሰራጨ ያለው ዜና ከዘጠኝ አመት በፊት የተሰራ ዘገባ ነው ሪፖርተር ጋዜጣ የዛሬ ዘጠኝ አመት ገደማ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለፌዴራል መንግሥት በጀት መሸፈኛ ካበደረው ገንዘብ ውስጥ ያልተመለሰለት 92.1 ቢሊዮን ብር መድረሱን ዘግቦ ነበር። ጋዜጣው በዘገባው ላይ ባንኩ በቀጥታ ለማዕከላዊ መንግሥት አበድሮ ያልተመለሰለት ገንዘብ 83.2 ቢሊዮን ብር ወይም 90.3 በመቶ ሲሆን፣ ቀሪው 9.7 በመቶ ደግሞ በቦንድ ተበድሮ ያልተመለሰለት መሆኑን ጠቅሶ ነበር። ይሁንና ይህ የሪፖርተር ዘገባ የታተመበት ጋዜጣ የስክሪን ቅጂ (ስክሪንሾት) ከሰሞኑ በስፋት እየተጋራ ሲሆን መረጃው አዲስ እንደሆነ ተደርጎ እየቀረበ መሆኑን ኢትዮጵያ ቼክ ተመልክቷል። ይሁንና መረጃው አዲስ ሳይሆን እ.አ.አ በፌብሪዋሪ 21/2016 የወጣ ዜና መሆኑን ማየት ችለናል። ላለፉት 16 ዓመታት ያለገደብ ከብሔራዊ ባንክ ገንዘብ ሲበደር የነበረው የፌደራል መንግሥት ከአገር ውስጥ ገቢ ከ15 በመቶ የበለጠ ገንዘብ በብድር ማግኘት እንዳይችል የሚገድብ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከወራት በፊት መቅረቡ ይታወሳል። ለምክር ቤቱ የቀረበው የብሔራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅ መንግሥት የተበደረውን ገንዘብ በአንድ ዓመት ውስጥ ካልመለሰ ከተቋሙ ሌላ ብድር መውሰድ እንደማይችልም ያስቀመጠ ነው። ኢትዮጵያ ቼክ