
Rhapsody Global Club ( Mandate 1B ROR Influences )
February 28, 2025 at 09:35 PM
Rhapsody Amharic
Sat Mar 01 2025
የዮሐንስ ራዕይ
"ትዕግሥትም ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም" (ያዕቆብ 1:4) ።
ከላይ ባለው ጥቅስ ውስጥ እንድታስተውሏቸው የምፈልገው ሁለት ቁልፍ ቃሎች አሉ፤ እነርሱም "ፍጹማን" እና "ምሉዓን" የሚሉት ናቸው። "ፍጹማን" የሚለው ቃል የመጣው "ቴሌዮስ" ከሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን ፍችውም ሙሉ ወይም የተጠናቀቀ ማለት ነው። በሌላ በኩል ደግሞ "ምሉዓን" ተብሎ የተተረጎመው "ሆሎክለሮስ" ከሚለው ከግሪኩ ቃል ነው ትርጉሙም፣ በሁሉም ነገር ሙሉ፤ የተሟላ፣ ፍጹም፣ ማንኛውም የሚያስፈልግ ነገር ያልጎደለበት ማለት ነው ። የእግዚአብሔር ፈቃድ ለእናንተ ይህ ነው።
በቆላስይስ 4:12 ላይ፣ መንፈስ፣ በሐዋርያው ጳውሎስ በኩል አንድ አስደናቂ ነገር ይነግረናል። እንዲህ አለ "ከእናንተ የሆነ የክርስቶስ ባሪያ ኤጳፍራ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ተረድታችሁና ፍጹማን ሆናችሁ እንድትቆሙ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ በጸሎቱ ይጋደላል።" በድጋሚ፣ እዚህ ላይ ያለው "ፍጹማን" የሚለው ቃል "ቴሎዮስ" የሚለው የግሪኩ ቃል ነው። ከዚያም ጳውሎስ አዲስ ቃል "ፕሌሮ" (ግሪክ) የሚልን ቃል ተጠቅሟል፣ ትርጉሙም "ሙሉ በሙሉ" (ሁሉን) የሚል ነው።
"ፕሌሮ" ማለት ሙሉ የሆነ፣ ተሟልቶ የቀረበ ወይም እስከ አፍጢሙ የሞላ ማለት ነው። በተጨማሪም፣ ሙሉነትን፣ አንድን ዓላማ ማሳካትን ወይም አንድን ነገር ወደ ፍጻሜ ማምጣትን ያመለክታል። ይህ አንድ አስፈላጊ ጥያቄን ያስነሳል ይሄውም እስከ አፍጢሙ የሚሞላው ወይም ተሞልቶ የሚቀርበም በምንድን ነው? በቆላስይስ ያሉ ክርስቲያኖች፣ በፈቃዱ እውቀት፣ መንፈሳዊ ጥበብንና አእምሮ ሁሉ እንዲሞሉ በቆላስይስ 1:9 ላይ ጳውሎስ የጸለየውን ውብ የሆነ የመንፈስ ጸሎት ያስታውሰናል: - "ስለዚሁ እኛ ደግሞ ይህን ከሰማንበት ቀን ጀምረን የፈቃዱ እውቀት መንፈሳዊ ጥበብንና አእምሮን ሁሉ እንዲሞላባችሁ እየለመንን፥ ስለ እናንተ ጸሎትን አልተውንም።"
ቀጥሎ ያለው ቁጥር 10 በፈቃዱ እውቀት መንፈሳዊ ጥበብንና አእምሮ መሞላት የሚያስፈልበትን ምክንያት ይነግረናል: - "በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ" (ቆላስይስ 1:10-11) ። እስቲ አስቡት! እግዚአብሔር ፍጹማን እና ምሉዓን እንድትሆኑ ይፈልጋል፤ በእርሱ ፈቃድ እውቀት የተሞላችሁ፣ ፍጹም የሆናችሁ፣ ተሞልታችሁ የቀረባችሁ እንድትሆኑ የሚፈልገው በእግዚአብሔር እውቀት በጨመራችሁ ቁጥር ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ፣ በሁሉም ነገር እርሱን ደስ የሚያሰኝ ሕይወት ትኖሩ ዘንድ እና በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ ታፈሩ ዘንድ ነው። ሃሌሉያ!
Prayer / Confession
ውድ አባት ሆይ፣ ስለሚለውጠኝ እና ከፍጹም ፈቃድህ ጋር እንድስማማ ስለሚያደርገኝ ቃልህ አመሰግንሃለሁ። በአንተ እውነት ላይ ሳሰላስል ሙሉ ወደመሆን እና ወደ ሙላት በመንፈስህ እየተመራሁ ለሕይወቴ ካለህ ዕቅድ ሁሉ ጋር ፍጹም እና ሙሉ ሆኜ እቆማለሁ፤ እኔ ምንም ነገር አይጎድልብኝም እናም ለስምህ ክብርን አመጣለሁ። በኢየሱስ ስም። አሜን።
Further study
2 ኛ ጢሞቴዎስ 3:16-17; ኤፌሶን 3:19; ኤፌሶን 4:13
1-year bible reading plan
የማርቆስ ወንጌል 9:14-32 & ኦሪት ዘህልቁ 7-8
2-year bible reading plan
የማቴዎስ ወንጌል 19:1-12 & ኦሪት ዘጸአት 10
WhatsApp Chanel for rhapsody Translation :
https://whatsapp.com/channel/0029Va9SJ9OHFxP0Xh4KCN3F