AFRICA TV1
AFRICA TV1
February 18, 2025 at 02:47 PM
አላህ(ሱ·ወ) ከፍጥረታቱ የወደዳቸውን መርጦ ለኢማን መርቷቸዋል። ከአማኞች ደግሞ ኡለማዎችን መርጦ ችሮታውን ውሎላቸዋል። በሁሉም ዘመንና ግዜ ከተቀሩት አማኞች በላጮች አደረጋቸው። በዕውቀት አነሳቸው፣በትእግስት አስዋባቸው፣በነርሱ ሀላል ከሀራም፣ሀቅ ከባጢል፣ጠቃሚ ከጎጂ እና ጥሩ ከመጥፎ ተለይቶ ይታወቃል።በኡለሞች ዝንጉ ይገሰፃል ፣አላዋቂ ይማራል……በውብ ምክራቸው አምልኮን የሚያጓድል ይገሰፃል :: እነሆ በሀገራችን ኢትዮጵያ በሚገኙ ዕውቅ የቁርዓን ሙፈሲር ኡለሞች የሚቀርበው እና የቁርዓን መልዕክቶች በሚያምርና ግልጽ በሆነ አቀራረብ የሚቀርብበት "በይናት" የተሰኘ ልዩ ፕሮግራም 5ኛ ምዕራፉን ወደናንተ ወድ ተመልካቾች ይዞላችሁ ይቀርባል።በዚህ ፕሮግራም የቁርዓን መልክቶች ውብ እና ማራኪ በሆነ አቀራረብ ይተነተኑበታል፡፡ፕሮግራሙን በአፍሪካ ቲቪ በቀርብ ቀን በተቀደሰው ወር ረመዳን ይጠብቁ። #በረመዳን_ይጠብቁን #ቁርኣን_የህይወት_ጎዳና #በይናት አፍሪካ ቲቪ1 ናይል ሳት 📡🛰 ፍሪኩዌንሲ 11636 ሲምቦል ሬት 27500 ፖላራይዜሽን፡ ቨርቲካል

Comments