
AFRICA TV1
February 18, 2025 at 05:43 PM
የሰው ልጆች ከነበሩበት የጨለማ ህይወት ተላቀው ፣ ቅናቻን ተጎናፅፈው ፣ የህይወት መንገዳቸውን ተመርተው ፣ የሁለት ዐለም ስኬትን እንዲቸሩ ልዕለ ሀያሉ ፈጣሪ ንግግሩን መመሪያ ይሆነን ዘንድ በተከበረው ወርሀ-ረመዳን አወረደልን። አጥብቀንም እንድንይዘው አዘዘን። ሁሌም የያዘው ከፍ የተወው ደሞ ዝቅ እንደሚል ነገረን።
'ፉርቃን' በሚል ቁርዐናዊ ርዕስ ተውቦ በቁርዐን ወር ስለ ቁርዐን ከተለያዩ የቁርዐን ሰዎች ጋር እያወጋጋ ፣ ውብ ቲላዋዎችን እያስዳመጠ ፣ ደሳስ የሚሉ ገጠመኞችና ተሞክሮዎችን በምልሰት እያስቃኘ ፤ እያዝናና ፤ ቁም ነገር እያስጨበጠ በአፍሪካ ቲቪ ወሩን ሙሉ ከእናንተ ጋር ይቆያል።
#ፉርቃን
#በረመዳን_ይጠብቁን
#ቁርዐን_የህይወት_ጎዳና