Rhapsody Global Club ( Mandate 1B ROR Influences )
Rhapsody Global Club ( Mandate 1B ROR Influences )
June 12, 2025 at 05:26 PM
Rhapsody Amharic Fri Jun 13 2025 ጸንታችሁ ቁሙ፤ ማመቻመችን እምቢ በሉ በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም። (ኢሳይያስ 43፡2) ከወንጌል የተነሳ ራሳችሁን በሁሉም አቅጣጫ በግፊቶችና በከሳሾች የተጫናችሁ ሆናችሁ ታገኙት ይሆናል፤ ነገር ግን ተስፋ አትቁረጡ። የምታደርጉት ሁሉ የወደ ፊት ተስፋ አለው። በጌታ ያላችሁ ጥረት ሁሉ በከንቱ አይደለም፤ አላማ ያለው እና ዘላለማዊ ነው። ሁሉም ነገር የተደላደለ ወይም ተግዳሮት የሌለ እንደሚሆነ ጌታ በፍጹም ቃል አልገባልንም። ችግሮች፣ ፈተናዎ እና አሳዳጆች እንዳሉ ነግሮናል። ነገር ግን በዚህ ሁሉ መሀል፣ ስለ መገኘቱ እና ስለ ድሉ ማረጋገጫ ሰጥቶናል። በመክፈቻ ጥቅሳችን ላይ ያነበብነውን አስታውሱ፤ ፈተና ወይም እሳት የለም አላለም። የገባልን ቃል ተግዳሮቶች የሉም ማለት ሳይሆን በእነዚያ ችግሮች መሀል የእርሱ መገኘት እና ለእናንተ ጥበቃ ማድረግ ነው።(ያዕቆብ 1፡2) ላይ “. . .ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት” ያለበትን ምክንያት ይህን እንድትረዱ ይረዳችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ በዳንኤል 3 ላይ ስለ ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ፣ ሶስቱ ወጣቶች በገጠማቸው አስከፊ ተቃርኖ መካከል እንዴት በእምነት ጸንተው እንደቆሙ ይነግረናል። ሁልጊዜ እየታወሰ የሚኖረው ታሪካቸው የእሳት ግለቱ እና ተዓምራዊ በሆነ መንገድ ማመለጣቸው ነው፣ ነገር ግን ከዚህ የበለጠ ነገር አለው። ወደ እሳት ነበልባሉ ከመጣላቸውአስቀድሞ ኩኔንን፣ መገለልን እና የውሸት ክሶችን ገጥመዋል። ጥላቻውንና ተቃውሞውን በቀላሉ የተቋቋሙበት ምክንያት እምነታቸውን ማመቻመች እምቢ በማለታቸው ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡17 እንዲህ ይላል፤ “ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤” ስለዚህ፣ እግዚአብሔር የሰጣችሁን መልካም ህይወት ለመኖር፣ መጋፈጥ ያለባችሁ፣ በውስጡ ማለፍ ያለባችሁ፣ ተቋቁማችሁ እና ተጋጥማችሁ ማለፍ ያለባችሁ ነገሮች አሉ። ምናልባት በሁሉም አቅጣጫ ጠላቶች ይኖሩ ይሆናል፤ ነገር ግን በእነዚህ ሁሉ መሀል፣ ከአሸናፊዎች ትበልጣላችሁ። 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡12 ላይ እንዲህ ይላል፤ “በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ።” በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና (1ኛ ዮሐንስ 4፡4)። በማቴዎስ 28፡20 ላይ አረጋግጧል፤ “እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።” አይናችሁን ወደ ፊት ወደሚሆነው እና በክብሩ ላይ አድርጉ። በጊዜዊ ተግዳሮቶች መሰናከልን እምቢ በሉ። ምንም ይሁን ምን፣ ቃሉ በህይወታችሁ እንደሚያሸንፍ እና ክብሩ ሁል ጊዜ በእናንተ ውስጥ እና በእናንተ በኩል እንደሚገለጥ እርግጠኛ ሁኑ። Prayer / Confession ታላቁ እርሱ በእኔ ውስጥ ስለሚኖር፣ ከተግዳሮቶች ወይም ከተቃውሞች ይልቅ፣ በእምነት ጸንቼ ቆማለሁ። ቃልህ ከፈተናዎች ሁሉ የበላይ ያደርገኛል፣ እናም በፍጹም ድል ውስጥ እራመዳለሁ። ስለመገኘትህ፣ ስለጥበቃህ እና ስለማይወድቀው ቃልህ አመሰግናለሁ። በኢየሱስ ስም። አሜን። Further study 1 ኛ ቆሮንጦስ 15:57-58; ሮሜ 8:31-37; 2 ኛ ቆሮንጦስ 4:17 AMPC 1-year bible reading plan የሐዋርያት ስራ 4:1-31 & መጽሀፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 16-19 2-year bible reading plan የሉቃስ ወንጌል 1:26-38 & ኦሪት ዘዳግም 11 WhatsApp Chanel for rhapsody Translation : https://whatsapp.com/channel/0029Va9SJ9OHFxP0Xh4KCN3F
❤️ 1

Comments