Rhapsody Global Club ( Mandate 1B ROR Influences )
Rhapsody Global Club ( Mandate 1B ROR Influences )
June 13, 2025 at 07:04 PM
Rhapsody Amharic Sat Jun 14 2025 የራዕይ እና የሃሳብ ሃይል ያዕቆብም ልብን ለውዝ ኤርሞን ከሚባሉ እንጨቶች እርጥብ በትርን ወስዶ በበትሮቹ ውስጥ ያለው ነጭ እንዲታይ ነጭ ሽመልመሌ አድርጎ ላጣቸው። (ዘፍጥረት 30፡37) በዘፍጥረት 30 እና 31 ላይ ያለው የያዕቆብ ታሪክ ውብ የሆነ የዕይታ ኃይልና ና የፈጠራ ችሎታን አስደናቂ ማሳያ ነው። ያዕቆብ ላባን ለማገልገል ሲስማማ፣ ቃል የተገባለት ደመወዝ ከብቶች ነበሩ። ቢሆንም፣ ላባ በተደጋጋሚ ሀሳቡን በመቀየር ያዕቆብ አታለለው። ነገር ግን ያዕቆብ፣ በመለኮታዊ ጥበብ እና በፈጣራ ስልት፣ ሁኔታውን ቀየረው። ያዕቆብም ልብን ለውዝ ኤርሞን ከሚባሉ እንጨቶች እርጥብ በትርን ወስዶ በበትሮቹ ውስጥ ያለው ነጭ እንዲታይ ነጭ ሽመልመሌ አድርጎ ላጣቸው። የላጣቸውንም በትሮች በጎቹ ውኃ ሊጠጡ በመጡ ጊዜ በውኃ ማጠጫው ገንዳ ውስጥ በበጎቹ ፊት አኖራቸው። በጎቹም በበትሩ ፊት ግንኙነት ባደረጉ ጊዜ፣ ያዕቆብ በትክክ ይፈለገው እንደነበረው አይነት ግልገሎች ወለዱለት። ከዚያ በኋላ ያዕቆብ እነዚያን በትሮችን አልፈለጋቸውም። ያዕቆብም ጠቦቶቹን ለየ፥ ሽመልመሌ መሳይና ጥቁር ያለባቸውን በጎቹንም ሁሉ በትልቆቹ በጎች ፊት ለፊት አኖረ። ይህንን በማድረግ ለመንጎቹ ራዕይን ፈጠረ፤ እነሱም ባዩት መልክ ጠቦቶችን ፈጠሩ። የያዕቆብ ዜዴ የራዕይን የመፍጠር ሃይልን ሰርቶ ማሳየትን ነበር። የሃሳብ ጉልበቱን በመጠቀም ውጤቱ ላይ ተጽዕኖ አድርጓል። ጠንካሮችሁ በጎች ሲጸንሱ፣ ያዕቆብም በትሩን በአይናቸው ፊት አደረገ፤ እነሱም ጠንካሮችን፣ ተፈላጊነት ያለው ዘር እንደሚፈጥሩ እርግጠኛ ነበር። በጎቹ ደካማ በሆኑ ወቅት በትሩን አልተጠቀመም፤ ስለዚህ እነዚያ ደካሞች የላባ ነበሩ። ከጊዜ በኋላ፣ የያዕቆብ መንጎች እየጠነከሩ እና የበለጠ መጠናቸው እየበዛ መጣ፤ ነገር ግን የላባ ደካማ ሆነው ቀሩ። የያዕቆብ ስኬት በመለኮታዊ መገለጥ ነው። በህልሙ አውራዎቹ ፍየሎች፣ ቡራቡሬዎቹ፣ እንደ ሽመልመሌ መሳይና ዝንጕርጕር ነቍጣም ያለበት በመንጋው ላይ ሲዘሉ አየ። መልአኩም እርሱ ያየውን ራዕይ አጸናው፤ እንዲህ አለ፤ “. . . ዓይንህን አቅንተህ እይ በበጎችና በፍየሎች ላይ የሚንጠላጠሉት የበጎችና የፍየሎች አውራዎች ሽመልመሌ መሳዮችና ዝንጕርጕሮች ነቁጣ ያለባቸውም ናቸው፤ . . . ።” (ዘፍጥረት 31፡12) ይሄ ምን ያህል አስፈላጊ ነው! ማየት በምትፈልጉት ነገር ላይ ትኩረታችሁን በማድረግ የምትሹትን ወደፊታችሁን የመፍጠር አቅም አላችሁ። በአዕምሯችሁ የምትፈልጉትን ራዕይ ፍጠሩ። በእናንተ ውስጥ በሚሰራው ቃል እና የመንፈስ ቅዱስ ሃይል መሰረት አካላዊ እውነታውን መፍጠር ወይም ቅርጽ ማስያዝ ትችላላችሁ። ሃሌ ሉያ! Prayer / Confession ውድ አባት ሆይ፣ በራዕይ እና በቃልህ ሃይል የምፈልገውን የወደፊቱን እንዳይ እና እንድፈጥር አቅሙን ስለሰጠኸኝ አመሰግናለሁ። የማሰብ ሃይሌን ስጠቀም እና በመንፈስህ ስነቃቃ፣ ከመለኮታዊ አላማህ ጋር በሚጣጣም መልኩ፣ በድል እና በሁሉ አቅጣጫ በመስፋፋት ህይወቴን እገነባለሁ። አለሜን ተጽዕኖ ለማድረግ እና ፍጻሜዬን ለማሟላት ሃይልን ታጥቅያለሁ። በኢየሱስ ስም። አሜን። Further study ኦሪት ዘፍጥረት 13:13-15; ትንቢተ ዕምባቆም 2:2; ኤፌሶን 3:20 1-year bible reading plan የሐዋርያት ስራ 4:32-5:1-11 & መጽሀፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 20-22 2-year bible reading plan የሉቃስ ወንጌል 1:39-56 & ኦሪት ዘዳግም 12 WhatsApp Chanel for rhapsody Translation : https://whatsapp.com/channel/0029Va9SJ9OHFxP0Xh4KCN3F
🙏 1

Comments