
GLC FAMILY!!!
2.4K subscribers
About GLC FAMILY!!!
”ጻድቃን እንደ ዘንባባ ይንሰራፋሉ፤ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ይንዠረገጋሉ። በእግዚአብሔር ቤት ተተክለዋል፤ በአምላካችንም አደባባይ ይንሰራፋሉ። ባረጁ ጊዜ እንኳ ያፈራሉ፤ እንደ ለመለሙና እንደ ጠነከሩም ይኖራሉ።“. መዝሙር 92:12-14 ይህ የክብር ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ይፋዊ የዋትስአፕ ገጽ ነው። ሌሎችም በዚህ ቻናል በሚተላለፉ ሕይወት ለዋጭ መልዕክቶች ይጥቀሙ ዘንድ ለብዙዎች ማካፋልዎን አይዘንጉ። ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ አንድ ቃል ሕይወትዎ ለዘላለም ይለወጣል!
Similar Channels
Swipe to see more
Posts

“ተስፋችሁ በመንፈስ ቅዱስ ኀይል እያደገ እንዲሄድ የተስፋ አምላክ በእርሱ በመታመናችሁ ደስታንና ሰላምን በሙላት ይስጣችሁ።” ወደ ሮም ሰዎች 15:13 አማ05 ይህ ሳምንት በዚህ የእግዚአብሔር ቃል ባረኳችሁ “ተስፋችሁ በመንፈስ ቅዱስ ኀይል እያደገ እንዲሄድ የተስፋ አምላክ በእርሱ በመታመናችሁ ደስታንና ሰላምን በሙላት ይስጣችሁ።” አሜን አሜን አሜን!!! ሬቨ ተዘራ ያሬድ መልካም ሳምንት


…..ሁሉም ከርሱ፣ በርሱ፣ ለርሱ!!!! ““እግዚአብሔር መልሶ እንዲሰጠው፣ ለእግዚአብሔር ያበደረ ከቶ ማን ነው?” ሁሉም ከርሱ፣ በርሱ፣ ለርሱ ነውና፤ ለርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን! አሜን።” ሮሜ 11:35-36 NASV በኛ ሕይወት የሆነው ሁሉ፣ ከርሱ፣ በርሱ፣ ለርሱ እንጂ ከእኛ በእኛ ለእኛ አይደለምና ክብር ለርሱ ይሁን በሉ!!! መልካም ቀን!!! ሬቨ ተዘራ ያሬድ


*…ክርስቶስ የእግዚአብሔር ኀይልና የእግዚአብሔር ጥበብ ነው!!!* “የዚህ ዓለም ሰዎች በገዛ ጥበባቸው እግዚአብሔርን ማወቅ እንዳይችሉ እግዚአብሔር በጥበቡ ዘጋባቸው፤ ነገር ግን እንደ ሞኝነት በሚቈጠረው እኛ በምናስተምረው ወንጌል የሚያምኑትን ለማዳን የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖአል። መቼም አይሁድ ተአምር ማየትን ይፈልጋሉ፤ የግሪክ ሰዎች ደግሞ ጥበብን ይሻሉ። እኛ ግን ክርስቶስ ስለ እኛ መሰቀሉን እናስተምራለን፤ ይህም ለአይሁድ መሰናከያ ነው፤ ለግሪክ ሰዎች ደግሞ ሞኝነት ነው። ለተጠሩት ግን ለአይሁድም ሆነ ለግሪክ ሰዎች፥ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ኀይልና የእግዚአብሔር ጥበብ ነው። ወንድሞቼ ሆይ! እግዚአብሔር በጠራችሁ ጊዜ ምን ዐይነት ሰዎች እንደ ነበራችሁ አስታውሱ፤ እንደ ሰው አስተሳሰብ ከእናንተ መካከል ብዙዎች ጥበበኞች ወይም ብርቱዎች ወይም ታላላቅ ሰዎች አልነበሩም።” 1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1:21-24, 26 አማ05 መልካም ቀን!!! ሬቨ ተዘራ ያሬድ
