DW Amharic
February 3, 2025 at 03:50 PM
ዶቼ ቬለ በኢትዮሳት ያድምጡ!
ውድ አድማጮች በተደጋጋሚ ላቀረባችሁት ጥሪ እነሆ ምላሽ እንዲሆን ዶቼ ቬለ የቀጥታ ሥርጭቱን በኢትዮ-ሳት ማስተላለፍ ጀምሯል።
የዶቼ ቬለን የቀጥታ ሥርጭች በኢትዮ-ሳት ወይንም (NSS-12) በ10985,0 ሜጋ ኸርዝ፣ ሆሪዞንታል፣ DW-08 ላይም ማድመጥ ይቻላል። ትራንስፖንደሩ፦ MEH01 ወይንም EAH01 ነው።
ከዚህ ቀደም ዶቼ ቬለ ከሚገኝባቸው አማራጭ የማድመጫ መስመሮች በተጨማሪ በጎርጎሪዮሳዊው አዲስ ዓመት 2025 ሥርጭቱንን በኢትዮሳት ላይም ማቅረብ መጀመሩን ሲገልጽ በደስታ ነው!
ፖለቲካዊ ፣ ማኅበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ ይዘት ያላቸውን ዝግጅቶች እና ዓለም አቀፍ ወቅታዊ የዜና ትንታኔዎች የሚያሰራጨው ዶቼ ቬለ አሁን አዲስ በጀመረው የኢትዮሳት የሳተላይት ማሠራጫ ከሰኞ እስከ እሑድ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር እንደተለመደው ከምሽት አንድ ሰዓት ጀምሮ ይደመጣል።
ሥርጭታችን በኢትዮሳት ላይ በጥራት ይደመጣል? አስተያየታችሁን ጻፉልን። ምናልባትም ስታደምጡ የሚያሳይ ፎቶም ብትልኩልን ደስ ይለናል።
ለገለልተኛና ወቅታዊ መረጃ ምርጫዎ ዶቼ ቬለ ይሁን!
ዶቼ ቬለን በኢትዮሳት ያድምጡ።
👍
1