
DW Amharic
February 4, 2025 at 12:00 PM
በጉጂ ዞን በመሬት መደርመስ የ8 ሰዎች ሕይወት አለፈ
በጎጂ ዞን ሳባ ቦሩ ወረዳ በባሕዊ መንገድ ማዕድን እያወጡ በነበሩ ሰዎች ላይ በደረሰ የመሬት መደርመስ የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ ኮሚኒኬሽን ገለጸ ። የዞኑ ኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ አሸናፊ ዳንቆ ለዲዳቢሊው እንደገለጹት በትናትናው ዕለት 9፡00 ገደማ አደጋው መድረሱን ገልጸው በቦታው በባሕላዊ መንገድ ሲያወጡ የነበሩ ሕይወታቸው ያለፈው 8ቱ ሰዎች አስከሬን ዛሬ መውጣቱን አመልክተዋል ፡፡
‹«ቦታው ጉጂ ዞን ሳባ ቦሩ ወረዳ ቃቲቻ የሚባል ቀበሌ ውስጥ ነው ፡፡ በትናንትናው ዕለት ከ9፡00 በኋላ ነው ድርጊቱ የተፈጠረው፡፡ በባሕላዊ መንገድ ማዕድን በማውጣት እየሠሩ የነበሩ ሰዎች ላይ የአፈር ክምር ተንሸራርቶ የስምንት ሰዎች ሕይወት አልፏል ፡፡ ሕይወታቸውን ለማሻሻል በባሕላዊ መንገድ የሚሠሩ ሰዎች ናቸው መሬቱ ተንሸራርቶ ነው ሕይወታቸው ያለፈው፥ አስከሬናቸው ወጥቷል›› ሲሉ ኃላዲው ተናግረዋል ።
ሳባ ቦሩ ወረዳ ከጉጂ ዞን አስተዳደር መቀመጫ ከሆነችሁ አዶላ ከተማ 70 ኪ.ሜ ገደማ ላይ የሚትገኝ ወረዳ ናት ፡፡
ፎቶ፦ ከጉጂ ዞን ኮሙኒኬሽን
ዘገባ፦ ነጋሣ ደሳለኝ ከአሶሳhttps://www.facebook.com/dw.amharic/posts/pfbid0bUpHAQPCN6o23AuaQ4FtdUiydBo1sNmEgwAHuUqvKZiZ1hia1ibauFW38cz2X5rnl
👍
😢
3