DW Amharic

DW Amharic

185.2K subscribers

Verified Channel
DW Amharic
DW Amharic
February 5, 2025 at 02:43 PM
በሶማሌ ክልል የሚታየውን ሙስና እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ ትኩረት እንዲሰጥ  የተቃዋሚ ፓርቲው ሶማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ ጠየቀ። በክልሉ ለህብረተሰቡ በድጎማ የሚቀርቡ ሸቀጦች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ከማድረግ ይልቅ የግለሰቦች መጠቀሚያ ናቸው ያለው ፓርቲው የክልሉ መንግስት ተገቢውን እርምጃ አልወሰደም ሲል ወቅሷል። ሶማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ዩሱፍ ሁሴን ለዶይቸ ቬለ በስልክ በሰጡት መረጃ ሀገራዊ ችግር ነው ያሉት ሙስና በክልሉ መንሰራፋቱን ገልፀዋል። በሌላ በኩል በክልሉ አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚሻ የጠቀሱትን  የመልካም አስተዳደር ችግር አብነት በማንሳት አስረድተዋል። የተቃዋሚ ፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ዩሱፍ በክልሉ ለህብረተሰቡ በድጎማ የሚቀርቡ ሸቀጦች የሚከፋፈሉበት መንገድ ትክክለኛ ያልሆነና የግለሰቦች መጠቀሚያ መሆኑን በመጥቀስ መንግስት መፍትሄ አልወሰደም ሲሉ ወቅሰዋል። በተመሳሳይ የነዳጅ ምርቶች ስርጭት በተለይ በጅግጅጋ ከተማ በጥቁር ገበያ ቁጥጥር ስር ውሏል ያሉት ሊቀመንበሩ በስርጭቱ ላይ "የህግ የበላይነት እየሰራ አይደለም በነዳጅ ዙርያ" ብለዋል ሲል መሳይ ተክሉ ከድሬዳዋ ዘግቧል።
👍 😮 3

Comments