
DW Amharic
February 5, 2025 at 03:10 PM
የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የኒኩሌር የጦር መሳሪያ እንድትታጠቅ አንፈቅድም አሉ። ፕሬዚደንቱ ይህን ያሉት መስተዳድራቸዉ ሥለኢራን የሚከተለዉን መርሕ ዛሬ በፊርማቸዉ ባፀደቁበት ወቅት ነው።
ትራምት አያይዘውም «ኢራን ታላቅና ስኬታማ አገር እንድትሆን እፈልጋለሁ፤ ይሁንና የኒኩሌር የጦር መሳሪያ ሊኖራት አይገባም» ሲሉ ተደምጠዋል።
ከኢራን ጋር የተረጋገጠ የኒኩለር የሰላም ስምምነት ሊኖር ይገባል ያሉት ፕረዚደንቱ ይህም ኢራንን በሰላም እንድታድግና እንድትበለጽግ ያደርጋታል ማለታቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግቧል።
😂
❤️
👍
💔
😢
8