DW Amharic

DW Amharic

185.2K subscribers

Verified Channel
DW Amharic
DW Amharic
February 8, 2025 at 05:14 PM
የየካቲት 01 ቀን 2017 የዓለም ዜና • በምሥራቃዊ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚንቀሳቀሱ ሁሉም ታጣቂ ቡድኖች በአፋጣኝ ግጭት እንዲያቆሙ የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ጥሪ አቀረቡ። • የሱዳን ጦር በሰሜናዊ ኻርቱም የሚገኘውን ካፎሪ ወይም ባሕሪ የተባለ ቁልፍ አካባቢ መልሶ መቆጣጠሩን አስታወቀ። • በሰሜናዊ ማሊ በሀገሪቱ ጦር እና የሩሲያው ቫግነር ቅጥረኛ ወታደሮች አጀብ በመጓዝ ላይ በነበረ የተሽከርካሪዎች ቅፍለት ላይ በተፈጸመ ጥቃት 32 ሰዎች መገደላቸውን ባለሥልጣናት ዛሬ ቅዳሜ ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ተናገሩ። • ሐማስ ሦስት ታጋቾችን፤ እስራኤል 183 ፍልስጤማውያንን በቀይ መስቀል በኩል ለቀቁ • ዩክሬን በሩሲያ ኩርስክ ግዛት አዲስ ጥቃት መጀመሯን ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ አረጋገጡ። https://t1p.de/7iyoc?at_medium=Messenger&at_campaign=WhatsApp-Channel&at_number=DW_Amharic&at_dw_language=am • ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቱሩዶ አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ካናዳን ወደ አሜሪካ ለመጠቅለል ያቀረቡት ሐሳብ ተጨባጭ እንደሆነ አስጠነቀቁ።
👍 1

Comments