DW Amharic

DW Amharic

185.2K subscribers

Verified Channel
DW Amharic
DW Amharic
February 13, 2025 at 12:12 PM
ባሕር ዳር-ዋግሕምራ አስተዳደር ጎርፍና ድርቅ ከ40 ሺሕ በላይ ሕዝብ አፈናቀለ በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ባለፈው ክረምት የነበረው ከፍተኛ ዝናብ ባስከተለው የምርት መቀነስና ድርቅ ምክንያት ከ40ሺህ በላይ ነዋሪ መፈናቅሉን አንድ የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል አስታወቁ።የወልድያ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ በብሔረሰብ አስተዳደሩ 4 ወረዳዎች ባደረገዉ ጥናት ደግሞ ከ100ሺህ በላይ ነዋሪዎች ለምግብ እጠረት ተጋልጠዋል። 3ኛ ቀኑን በያዘው የአማራ ክልል ምክር ቤት 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የተገኙ የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ተወካይ የምክር ቤት አባል ለምክር ቤቱ እንዳመለከቱት በብሔረሰብ አስተዳደሩ በተከሰተ ድርቅ ሠዎች ከተለያዩ ወረዳዎች አካባቢያቸውን እየለቀቁ እየተሰደዱነው፤ እንደተወካዩዋ እስካሁን 43ሺህ ነዋሪዎች ፀጥታቸው አስቸጋሪ ወደሆኑ አካባቢዎች ሸሽተዋል። የአማራ ክልል አደጋ መከላክልና ምግብ ዋስትና ማስተባብሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዲያቆን ተስፋው ባታብል በሰጡት መልስ “እንደዋግኽምራ ያሉ ዝናብ አጠር አካባቢዎች ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው፣ ተዘልለው የነበሩ ወረዳዎች ነበሩ አሁን ግ ን እርዳታው ተፈቅዶላቸዋል” ብለዋል፡፡ ኮሚሽነሩ አያይዘውም ዘላቂ መፍትሔ የሚሆነው መንግሥት ያስቀመጠውን ከተርጂነት የመውጣት አቅጣጫን መከተል ነው፡፡ በአማራ ክልል 2. 3 ሚሊዮን ያክል ሕዝብ የምግብ ርዳታ ፈላጊዎች ናቸዉ።ከነዚሕ ዉስጥ 665ሺህ ያክሉ ተፈናቃዮች መሆናቸውን ኮሚሽነሩ ገልጠዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የወልድያ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ በ4 ወረዳዎች ባደረገው የዳሰሳ ጥናት በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በአካባቢው ከነበርው ከባድ የክረምት ዝናብ ጋር ተያይዞ በ39 ሺህ 707 ሄክታር ላይ የተዘራ ሰብል ሙሉ በሙሉ ወድሟል።ሰብሉ በመዉደሙ 106 ሺህ 600 ነዋሪዎች ለካፋ ችግር መዳረጋቸውን ጥናቱ አረጋግጧል፡፡ 16ሺህ 88 ህፃናት ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ የአልሚ ምግብ እጥረት መጋለጣቸውን ጥናቱ ያሳያል። 10ሺህ 566 ነፍሰ ጡሮችና አጥቢ እናቶችም በችግር ላይ እንደሆኑ አመልክቷል። የዳሰሳ ጥናቱ አክሎም 8ሺህ 27 ሰዎች በወባ መጠቃታቸውን፣ 337 እንስሳትም መሞታቸውን ይፋ አድርጓል።ዓለም መኮንን እንደዘገበዉ ጥናቱ የተደረገዉ በደሀና፣ ፃግብጂ፣ ጋዝጊብላና ሰቆጣ ወረዳዎች ነዉ።

Comments