VOA Amharic
January 30, 2025 at 08:51 PM
ትላንት ረቡዕ ጥር 21 ቀን 2017 ዓ.ም በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል ቡድን የተሾሙ ግለሰብ በትግራይ ክልል የመቐለ ኤፍ ኤም ራድዮ ጣቢያን ለመቆጣጠር መሞከራቸውን የጣቢያው ጊዜያዊ ሥራ አስከያጅ ገለጹ። ድርጊቱን ፈጽመዋል የተባሉ ግለሰብ ላይም ጣቢያው ክስ መመስረቱን ተናገሩ።
https://amharic.voanews.com/a/mekele-fm-station-incident/7957402.html
ጣቢያውን ሊቆጣጠሩ ነበር በሚል ወቀሳ ከቀረበባቸው ፣ አቶ ዘመንፈስቅዱስ ፍስሃ ምላሽ ለማግኘት በእጅ ስልካቸው ላይ በተደጋጋሚ ደውለን ስብሰባ ላይ መሆናቸው ስለገለፁን ምላሻቸውን ማካተት አልቻልንም። 👉 ቪኦኤ አማርኛን በዋትስአፕ ይከታተሉ 👇
https://whatsapp.com/channel/0029VaYrYaWDjiOTnIzDG73B
👍
😮
😢
❤️
10