
VOA Amharic
12.6K subscribers
Verified ChannelAbout VOA Amharic
ቪኦኤ-አማርኛ በዲጂታል፣ በራዲዮና በቴሌቪዥን ዜናና ዘገባዎችን ለአድማጭና ለተመልካች ያቀርባል። https://amharic.voanews.com/
Similar Channels
Swipe to see more
Posts

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አህመድ ነገ ሐሙስ በሶማሊያ ጉብኝት በማድረግ ከሀገሪቱ ፕሬዝደንት ሃሳን ሼክ ሞሃሙድ ጋራ እንደሚወያዩ ከሶማሊያ ከመንግሥት ምንጮች መረጃውን ማግኘቱን ኤኤፍፒ አመልክቷል። https://amharic.voanews.com/a/abiy-ahmed-somalia/7988983.html ሁለቱ ሀገራት የሻከረውን ግንኙነታቸውን ለማደስ በመሞከር ላይ ባሉበት ወቅት የሚካሄደው ጉብኝት “በአንካራ የተፈጸመውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግና ለማጠናቀቅ ከሚደረጉ ሰፊ ጥረቶች አንዱ እንደሆነ” ዘገባው አመልክቷል። “በጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አህመድ የሚመራ ከፍተኛ የባለሥልጣኖች ቡድን ነገ ሞቃዲሹ እንደሚደርስ ይጠበቃል” ሲሉ ለፕሬዝደንታዊ ቤተ መንግሥቱ ቅርብ የሆኑና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ምንጭ መናገራቸውን ኤኤፍፒ በዘገባው አመልቷልክ።

ደቡብ አፍሪካ 127 የሚኾኑ ወታደሮቿን ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ አስወጥታለች፡፡ አራቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው መኾኑም ታውቋል። ወታደሮቹ ከሁለት ዓመታት በፊት የ16 ሀገራት ጥምር በሆነው በደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማኅበረሰብ ወይም ሳድክ ኅይል ውስጥ ታቅፈው፣ በሩዋንዳ ከሚደገፈው ኤም 23 ጋራ በመፋለም ላይ ያለውን የኮንጎ መንግሥት ለመደገፍ የተሠማሩ ነበሩ። https://amharic.voanews.com/a/s-africa-repatriates-more-than-120-soldiers-from-dr-congo/7988946.html ሃያ አንዱ ወታደሮች ትላንት ማክሰኞ የተመለሱ ሲሆን፣ 106 የሚሆኑት ደግሞ ዛሬ ረቡዕ ተመልሰው ደቡብ አፍሪካ ወታደሮቿን በሙሉ አስወጥታ አጠናቃለች፡፡ የተጎዱት ወታደሮች ወዲያውኑ ወደ ሆስፒታል ሲወሰዱ፣ ከተመለሱት ውስጥ አንዳንዶቹ የሥነ ልቦና ሕክምና እንደሚያስፈልጋቸውም ታውቋል።

📷:ዩክሬን፣ ኪቭ ውስጥ የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት በደረሰበት ቦታ የእሳት አደጋ ሠራተኞች በሥራ ላይ፣ የካቲት 19 ቀን 2017 ዓ.ም. 👉 በኪቭ እና ዶኔትስክ ክልሎች ቢያንስ ሰባት ሰዎች በሩስያ የአየር ጥቃት መገደላቸውን የዩክሬን ባለሥልጣናት ዛሬ አስታውቀዋል፡፡ የዶኔትስክ አስተዳዳሪ ቫዲም ፊላሽኪን በቴሌግራም ባስተላለፉት መልዕክት እንዳስታወቁት የሩስያ ኅይሎች ኮስትያንቲኒቭካ ከተማን ለማጥቃት 'ጋይድድ ቦምብ' የሚባሉትን የተወሰነ ዒላማ ላይ ተነጣጥረው የሚተኮሱ ፈንጂዎችን ተጠቅመዋል፡፡ በዚህም ቢያንስ አምስት ሰዎች መገደላቸውንና ስምንት መቁሰላቸውን የመጀመሪያ ደረጃ መረጃው እንደሚያሳይ ገልጸዋል። የኪቭ ክልል አገረ ገዥ ማይኮላ ካላሽኒክ በበኩላቸው የሩስያ ጥቃቶች ቢያንስ ሁለት ሰዎችን የገደሉ ሲሆን ሌሎች ሁለት ደግሞ ቆስለዋል ብለዋል።


አውሮፕላኑ የተከሰከሰው በቴክኒክ ችግር ሊሆን እንደሚችል ወታደራዊ ምንጮች ገልጸዋል። የሱዳን መገናኛ ጽሕፈት ቤትም በአደጋው ዐስር ሰዎች ቆስለዋል ብሏል። ✔️ ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/4hTFBZj

ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ወደ አሜሪካ መጥተው የሥራ ዕድልን መፍጠር ለሚሹ የውጪ ባለሃብቶች ለመኖሪያ ፈቃድ የሚያገለግላቸውን እና ‘ጎልድ ካርድ’ ብለው የሰየሙትን በ5 ሚሊዮን ዶላር መሸጥ እንደሚሹ አስታውቀዋል። https://amharic.voanews.com/a/us-trump-gold-cards/7988995.html በሁለት ሳምንታት ውስጥ እንዲጀምር በሚሹት የስደተኞች ፕሮግራም የሚሸጠው ‘ጎልድ ካርድ’ በቀጥታ የግሪን ካርድ ባለቤት እንደሚያደርግና ዜግነት ለማግኘት የሚደረግው ሂደት አካል እንደሚሆን አስታውቀዋል። ‘ጎልድ ካርድ’ ያላቸው ባለሀብቶች በአሜሪካ ለመሥራት፣ የሥራ ዕድልን ለመፍጠር ኩባንያዎችን ለመመስረትና እንዲችሉ እንዲሁም ታክስም እንደሚከፍሉ አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ “የኮሪደር ልማት” አወዛጋቢ ውጤቶች የነዋሪዎች አስተያየት በአዲስ አበባ የተመረጡ አካባቢዎች፣ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች በመከናወን ላይ ናቸው። ፕሮጄክቶቹ፣ የተሽከርካሪ እና የእግረኛ መንገዶችን፣ ልዩ የብስክሌት መንገዶችንና ሌሎችም የመሠረተ ልማት ውጤቶችን አስገኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል፣ የርእሰ መዲናዋ የረዥም ጊዜ ነዋሪዎች መፈናቀልና በመንገዶቹ ዳር ላይ ያሉ የንግድ ተቋማት መፍረስ፣ ከፕሮጀክቶቹ አወዛጋቢ ውጤቶች መካከል ኾነው ቀጥለዋል፡፡ በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞችም፣ መሰል “የኮሪደር ልማት” ፕሮጀክቶች ትግበራ፣ ተመሳሳይ ውጤቶችን እያስከተሉ በመከናወን ላይ ናቸው፡፡ አስተያየት ሰጪዎች ምን ይላሉ? ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ሊቀ ጳጳሱ ያጋጠማቸው ኢንፌክሽን ውስብስብ መሆኑን እና በሁለት እና ከዛ በላይ በሆኑ ረቂቅ ተሕዋያን አማካኝነት የተከሰተ መሆኑን የቫቲካን መግለጫ አመልክቷል። ✔️ ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/4bhc2ya