VOA Amharic
January 31, 2025 at 03:19 PM
ረቡዕ ምሽት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በረራ ላይ እያሉ በመጋጨታቸው ለ67 ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት የሆኑትን ሁለት አውሮፕላኖች ከወደቁበት የፖቶማክ ወንዝ ለማውጣት የሚደረገው ጥረት እንደቀጠለ ነው። https://amharic.voanews.com/a/recovery-mission-investigation-into-washington-plane-crash-continue/7958330.html
ከበርካታ የአሜሪካ ተቋማት የተውጣጡት መርማሪዎች፣ ከሄሊኮፕተር ጋር ተጋጭቶ ወንዙ ውስጥ በገባው የአሜሪካ አየር መንገድ ውስጥ የሚገኘውን እና "ጥቁሩ ሳጥን" በመባል የሚታወቀውን የበረራ መረጃ የሚያስቀምጥ መሳሪያ ማግኘት ችለዋል። ዋናተኞች ወደ ወንዙ ውስጥ ጠልቀው በመግባት ተጨማሪ የአውሮፕራኑን ስብርባሪ አካል ለማግኘት እንደሚሞክሩም የእሳት አደጋ መከላከያ ባለስልጣናት አመልክተዋል። 👉 ቪኦኤ አማርኛን በዋትስአፕ ይከታተሉ 👇
https://whatsapp.com/channel/0029VaYrYaWDjiOTnIzDG73B
👍
❤️
6