VOA Amharic
January 31, 2025 at 04:59 PM
በዲሞክራክቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በመንግሥት እና ኤም 23 በተሰኘው ታጣቂ ቡድን መካከል የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም፣ አስቸኳይ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ አባል ሀገራት አመራሮች ጥሪ አቅርበዋል።
በአካባቢው የሚገኙ የረድኤት ተቋማት ግጭቱ በቀጠናው ቀድሞውንም አስከፊ የነበረውን እና ለረጅም ጊዜ የዘለቀውን ሰብዓዊ ቀውስ የበለጠ እያባባሰው ነው ብለዋል። https://amharic.voanews.com/a/east-african-leaders-call-for-ceasefire-in-drc-as-fighting-worsens-humanitarian-crisis/7958461.html
የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ረቡዕ ምሽት በድረ ገፅ አማካኝነት በመሩት ስብሰባ ላይ የሰባት አባል ሀገራት መሪዎች የተገኙ ሲሆን፣ የኮንጎው ፕሬዝዳንት ፊሊክስ ቲሺሴኬዲ ግን በስብሰባ ሳይሳተፉ ቀርተዋል። 👉 ቪኦኤ አማርኛን በዋትስአፕ ይከታተሉ 👇
https://whatsapp.com/channel/0029VaYrYaWDjiOTnIzDG73B
👍
2