VOA Amharic

VOA Amharic

12.6K subscribers

Verified Channel
VOA Amharic
VOA Amharic
January 31, 2025 at 07:31 PM
በሶማሊያ የፑንትላንድ ባለሥልጣናት በቦሳሶ ከተማ የሚገኙና የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ሰነድ የሌላቸውን በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን እንዲያዙ አድርገዋል። ወደ ሀገራቸው እንደሚመልሱም አስታውቀዋል። እርምጃው ሰነድ አልባ የውጪ ዜጎችን ከሀገሪቱ የማስወጣት ዘመቻ አካል እንደሆነም ተመልክቷል። የተያዙት ስደተኞች በመኪና ተጭነው ከከማዋ ውጪ ተወስደዋል። ይህም ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ በማሰብ ሳይሆን እንዳልቀረ ተነግሯል። https://bit.ly/3PV9Pie እርምጃው የተወሰደው ፑንትላንድ በአይሲስ ላይ ወታደራዊ ዘመቻ በማካሄድ ላይ ባልችበት ወቅት ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት አንድ በአይሲስ አባልነት የተጠረጠረን ግለሰብ የፀጥታ ኅይሎች ተኩሰው መግደላቸውን ተከትሎ ነው። የተያዙት ስደተኞች ከሽብር እንቅስቃሴ ጋራ ግንኙነት ይኖራቸው ባለሥልጣናት ማስረጃ አላቀረቡም። ዩሱፍ ሞሐመድ ዩሱፍ ያጠናቀረውን ዘገባ እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል። 👉 ቪኦኤ አማርኛን በዋትስአፕ ይከታተሉ 👇 https://bit.ly/4eKIQjm

Comments