
VOA Amharic
February 2, 2025 at 12:01 AM
👉 ፑንትላንድ ሰነድ አልባ ኢትዮጵያውያንን ያዘች በሶማሊያ የፑንትላንድ ባለሥልጣናት በቦሳሶ ከተማ የሚገኙና የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ሰነድ የሌላቸውን በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን እንዲያዙ አድርገዋል። ወደ ሀገራቸው እንደሚመልሱም አስታውቀዋል። እርምጃው ሰነድ አልባ የውጪ ዜጎችን ከሀገሪቱ የማስወጣት ዘመቻ አካል እንደሆነም ተመልክቷል። የተያዙት ስደተኞች በመኪና ተጭነው ከከማዋ ውጪ ተወስደዋል። ይህም ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ በማሰብ ሳይሆን እንዳልቀረ ተነግሯል።
እርምጃው የተወሰደው ፑንትላንድ በአይሲስ ላይ ወታደራዊ ዘመቻ በማካሄድ ላይ ባልችበት ወቅት ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት አንድ በአይሲስ አባልነት የተጠረጠረን ግለሰብ የፀጥታ ኅይሎች ተኩሰው መግደላቸውን ተከትሎ ነው።
https://bit.ly/3PV9Pie
የተያዙት ስደተኞች ከሽብር እንቅስቃሴ ጋራ ግንኙነት ይኖራቸው ባለሥልጣናት ማስረጃ አላቀረቡም።
😮
❤️
👍
7