VOA Amharic

VOA Amharic

12.6K subscribers

Verified Channel
VOA Amharic
VOA Amharic
February 4, 2025 at 08:04 PM
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በኬንያ እያካሔደው ነው የተባለውን ሕገወጥ እንቅስቃሴ እና ወንጀሎች ለማስቆም፣ የኬንያ ፖሊስ በድንበሩ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ የሰራዊቱ አባላት ላይ ርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስታወቀ። የኢትዮጵያ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትም ከኬንያ መንግሥት ጋራ ተቀናጅቶ በሰራዊቱ ላይ ርምጃ መውሰድ መጀመሩን አረጋግጧል። የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በበኩሉ አባላቱ ፈፀሙ የተባሉትን ወንጀል እንደማይፈፅሙ ገልፆ፣ በወንጀል ትስስሮች ውስጥ ተሳታፊ ሆነው ከተገኙ ግን ርምጃ ለመውሰድ ቃል ገብቷል። https://amharic.voanews.com/a/kenya-operation-against-ola/7962773.html የኬንያ ፖሊስ፣ በማርሳቢት እና ኢሲኦሎ አውራጃዎች በሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ታጣቂዎች ላይ ያነጣጠረ የጸጥታ ርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስታውቋል። የኬንያ ፖሊስ ጉዳዩን አስመልክቶ በአወጣው መግለጫ፣ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት "በኬንያ ብሔራዊ ደኅንነት ላይ ከፍተኛ ስጋት የደቀኑ የወንጀል ድርጊቶች ውስጥ ተሳትፎ አለው" ሲል ከሷል። 👉 ቪኦኤ አማርኛን በዋትስአፕ ይከታተሉ 👇 https://bit.ly/4eKIQjm
⌛️ 1

Comments