VOA Amharic
February 4, 2025 at 08:31 PM
ዋሽንግተን የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ የዓለም አቀፍ ልማት ተራድዖ ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት ሠራተኞች ከትላንት ሰኞ ጀምሮ ሥራ እንዳይገቡ ታዝዘዋል።
መመሪያው ለሠራተኞቹ የተሰጠው ትላንት ሰኞ ሲሆን በፕሬዝደንቱ ፈቃድ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶችን አሠራር እንዲመረምሩ ልዩ ኅላፊነት የተሰጣቸው ቢሊዮነሩ ኢላን መስክ "መሥሪያ ቤቱ እንዲዘጋ ፕሬዝደንቱ ተስማምተዋል" ብለው ማስታወቃቸውን ተከትሎ እንደሆነ ተመልክቷል። መስክ ትላንት ማለዳ በኤክስ ማኅበራዊ መገናኛ የቀጥታ ውይይት መድረክ ኤክስ ስፔስ ላይ ሲናገሩ "ከፕሬዝደንቱ ጋር ስድስት አስርት ዓመታት ስላስቆጠረው ተቋም ስንወያይ መዘጋት እንዳለበት ተስማምተዋል" ብለዋል።
https://amharic.voanews.com/a/us-trump-usaid/7962840.html
መስክ" ተቋሙ አንድ ትል ያለበት አፕል ሳይሆን እንዳለ በትላትል የተወረሰ በመሆኑ ሊጠገን ስለማይችል መወገድ ነው ያለበት። እንዘጋዋለን" ማለታቸው ተጠቅሷል።
የአሜሪካ የዓለም አቀፍ ልማት ተራድዖ ድርጅት (ዪ ኤስ ኤ አይ ዲ) 120 በሚሆኑ ሀገሮች የሚካሄዱትን የሰብዐዊ ርዳታ፥ የልማት እና የጸጥታ መርሀ ግብሮች የሚቆጣጠር ሲሆን ኢላን መስክ፥ ፕሬዚደንት ትረምፕ እና አንዳንድ ሪፐብሊካን የምክር ቤት አባላት ለዘብተኛ (ሊበራል ) ዓላማዎችን ያራምዳል ብለው አጥብቀው በመወንጀል አነጣጥረውበታል ። 👉 ቪኦኤ አማርኛን በዋትስአፕ ይከታተሉ 👇
https://bit.ly/4eKIQjm
🙏
1