VOA Amharic
February 4, 2025 at 08:34 PM
አሜሪካ በካናዳ እና ሜክሲኮ ላይ የ25 በመቶ ታሪፍ ለመጫን መወሰኗ እና ሁለቱ ሃገራትም በምላሹ ተመሳሳይ ርምጃ እንደሚወስዱ ማስታወቃቸው፣ እንዲሁም ቀድሞውንም በቻይና ላይ ተጭኖ የነበረውን 10 በመቶ ታሪፍ ጨምሮ፣ በዓለም የንግድ ጦርነትና የኢኮኖሚ ቀውስ ይከሰታል የሚል ከፍተኛ ስጋት አሳድሮ ነበር። ፕሬዝደንት ትረምፕ አዲሱ ደንብ ተግባራዊ ከመሆኑ አንድ ቀን ቀደም ብሉ፣ ከካናዳ እና ከሜክሲኮ መሪዎች ጋራ መነጋገራቸውን ተከትሎ፣ ነገሮች ወደነበሩበት የተመለሱ መስለዋል። https://amharic.voanews.com/a/american-affairs/7962874.html
👍
🥹
2