
VOA Amharic
February 5, 2025 at 05:12 PM
ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ አሜሪካ ጋዛን በባለቤትነት መቆጣጠር እንደምትሻ አስታውቀዋል። ከዚህ ቀደም ፕሬዝደንቱ ጦርነት ባፈራረሳት ሰርጥ ውስጥ የሚኖሩ ፍልስጤማውያን ወደ ጎረቤት ጆርዳን እና ግብጽ ሄደው እንዲሰፍሩ ሐሳብ አቅርበው ነበር።
የፍልስጤም ራስ ገዝ፣ ግብጽ፣ ሳዑዲ አረቢያና ሌሎችም የአሜሪካ ሸሪኮችም ሆነ ወዳጅ ያልሆኑ ሃገራት የትረምፕን ሃሳብ ተቃውመዋል።
https://amharic.voanews.com/a/us-gaza/7963982.html
“ያነጋገርኳቸው ሰዎች በሙሉ አሜሪካ ጋዛን በባለቤትነት ትያዝ የሚለውን ሐሳብ ወደውታል። ድንቅ የሆነውን ሥፍራ በማልማትም በሺሕ የሚቆጠር የሥራ ዕድል ይፈጠራል” ብለዋል ትረምፕ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ምኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋራ በመሆን ዋሽንግተን ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ። 👉 ቪኦኤ አማርኛን በዋትስአፕ ይከታተሉ 👇
https://bit.ly/4eKIQjm
⌛️
❤️
2