VOA Amharic

VOA Amharic

12.6K subscribers

Verified Channel
VOA Amharic
VOA Amharic
February 7, 2025 at 05:14 PM
የጅቡቲ መንግሥት በአፋር ክልል ሲያሩ ቀበሌ ነዋሪዎች ላይ በድሮን አድርሶታል ያለውን ጥቃት በጥብቅ እንደሚያወግዙ በአፋር ክልል የሚገኙ የተፎካካሪ ፓርቲዎች አስታወቁ፡፡ የአፋር አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር እና የአፋር ለዴሞክራሲ እና ፍትሕ ፓርቲ በአወጡት መግለጫ፣ "ድርጊቱ ሰላማዊ ሰዎችን ዒላማ ያደረገ እንዲሁም የሀገር ሉአላዊነትን የተዳፈረ ነው" ሲሉ ወንጅለውታል፡፡ በጥቃቱ ስምንት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን ዘጠኝ የሚኾኑት ደግሞ ከባድና ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው መግለጫውን ካወጡት ተፎካካሪ ፓርቲዎች አንደኛው ለአሜሪካ ድምጽ አስታውቋል። https://amharic.voanews.com/a/afra-/7966793.html?withmediaplayer=1 በሆስፒታሉ ውስጥ በድሮን ጥቃቱ ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና በማግኘት ላይ መሆናቸውን የነገሩን የሲያሩ ቀበሌ ነዋሪዋ ወ/ሮ መሬም መሐመድ ጥቃቱ በድንገት መፈጸሙን ተናግረዋል፡፡ በጥቃቱ የወ/ሮ መሬም እህትን ጨምሮ ሌሎችም መገደላቸውን የተጎጅዋ ቤተሰብ እንደሆኑ የገለጹልን አብደላ መሐመድ ጠቁመዋል፡፡ 👉 ቪኦኤ አማርኛን በዋትስአፕ ይከታተሉ 👇 https://bit.ly/4eKIQjm
👍 ❤️ 💡 4

Comments