VOA Amharic

VOA Amharic

12.6K subscribers

Verified Channel
VOA Amharic
VOA Amharic
February 11, 2025 at 09:15 PM
በአማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ልዩ ስሙ "በርሚል ጊዮርጊስ" በተባለ የፀበል ስፍራ እንደገና ባገረሸው የኮሌራ ወረርሽኝ ሦስት ሰዎች መሞታቸውን የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል:: https://amharic.voanews.com/a/amhara-re-emerged-colera/7971293.html የተቋሙ ዳሬክተር አቶ በላይ በዛብህ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት ካለፈው ታኅሣሥ መጨረሻ ጀምሮ፣ በፀበል ስፍራው ወረርሽን ሦስት ሰዎች ሲሞቱ ከ200 በላይ የሚኾኑ ሰዎች በወረርሽኙ ተጠቅተው በጤና ተቋማት ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ አስታውቀዋል። እስከ ትላንት ድረስ በየቀኑ የበሽታው ተጠቂ በጤና ተቋማት እየተመዘገበ እንደሚገኝ የገለፁት ዳይሬክተሩ የፀበል ስፍራው በትንሹ ለ30 ቀናት ካልተዘጋ ወረርሽኙ ከክልሉ አልፎ በሀገር ከፍተኛ ደረጃ የከፋ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል። 👉 ቪኦኤ አማርኛን በዋትስአፕ ይከታተሉ 👇 https://bit.ly/4eK
❤️ 🥹 2

Comments