
VOA Amharic
February 18, 2025 at 05:25 PM
የትረምፕ አስተዳደር የፌዴራል አቪየሽን አስተዳደር ሠራተኞችን ማባረር ጀምሯል የትራንስፖርት ሚንስቴር "ወሳኝ የበረራ ደኅንነት ሠራተኞች አልተባረሩም" ብሏል
https://amharic.voanews.com/a/trump-begins-firings-of-faa-air-traffic-control-staff-just-weeks-after-fatal-dc-plane-crash/7979335.html
ሠራተኞቹን የማስወጣቱ ርምጃ የተጀመረው ቁጥሩ የበዛ ሰው በአውሮፕላን በሚጓጓዝበት ያለፈው ሳምንት መጨረሻ ከመኾኑም ሌላ ባለፈው ጥር ወር በሬገን ዋሽንግተን አውሮፕላን ጣቢያ ሁለት አውሮፕላኖች አየር ላይ ተጋጭተው የበርካታ ሰዎች ህይወት ከጠፋበት አደጋ በሳምንታት ተከትሎ ነው።
የአቪየሽን ደኅንነት ባለሞያዎች ማኅበር ፕሬዝደንት ዴቪድ ስፔሮ ባወጡት መግለጫ ወደ ቋሚ ሠራተኝነት መሸጋገሪያ ክትትል ወቅት ላይ ያሉ የቅርብ ጊዜ ተቀጣሪዎች "ከሥራ ተሰናብታችኋል" የሚለው የኢሜል ደብዳቤ የደረሳቸው ባለፈው ዓርብ ማታ መሆኑን አመልክተዋል።
ማንነቱ እንዳይገለጽ የጠየቀ የበረራ ትራፊክ ተቆጣጣሪ ለአሶሲየትድ ፕሬስ በሰጠው ቃል ከተባረሩት መካከል የራዳር ክትትል ባለሞያዎች እና አብራሪዎችን አውሮፕላን በማሳረፍ እና በበረራ ሂደት የሚረዱ ባለሞያዎች ጭምር እንዳሉባቸው ተናግሯል።
👍
❤️
🥹
15