VOA Amharic

VOA Amharic

12.6K subscribers

Verified Channel
VOA Amharic
VOA Amharic
February 18, 2025 at 07:21 PM
ካለፈው ዓመት ነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ ግልጽ በወጣ የፖለቲካ አመራሮች መከፋፈል ሳቢያ በድርጅታዊ ቀውስ ውስጥ የሚገኘውና ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋራ ፍጥጫ ውስጥ የገባው ህወሓት፣ 50ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን፣ ዛሬ የካቲት 11 ቀን አክብሯል። በአንጻሩ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ “የሕዝብን አንድነት ላለመበተን” በሚል፣ በመንግሥት የታቀደው የበዓሉ አከባበር መሰረዙን አስታውቋል። https://amharic.voanews.com/a/getachew-cancels-celebration/7979558.html የህወሓት ሊቀ መንበር ዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል በተገኙበት፣ ዛሬ ማክሰኞ በመቐለ ከተማ በተከናወነው የምሥረታ በዓሉ አከባበር ላይ፣ “የህወሓት ሕጋዊ ሰውነት አለመመለስ ወደ አላስፈላጊ ውጥረት የሚያስገባና የፕሪቶርያውን የሰላም ሰምምነትም አደጋ ላይ የሚጥል ነው፤” ብለዋል። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም፣ ለትግራይ ሕዝብ የእንኳን አደረሳችኹ መልእክት አስተላልፈዋል።
👍 ❤️ 😂 🥺 8

Comments