VOA Amharic

VOA Amharic

12.6K subscribers

Verified Channel
VOA Amharic
VOA Amharic
February 19, 2025 at 04:55 PM
የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በነጭ አባይ ግዛት በፈጸመው ጥቃት ጨቅላ ህፃናትን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሲቪሎች መሞታቸውን የሱዳን ባለሥልጣናት እና የመብት ተሟጋች ድርጅቶች ትላንት ማክሰኞ አስታወቁ። https://amharic.voanews.com/a/sudanese-rsf-paramilitaries-kill-100s-in-white-nile-state/7980677.html የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ “ቡድኑ ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በሱዳን ጦር ‘አሰቃቂ ሽንፈት’ ከደረሰበት በኋላ በአል-ጊታይና አካባቢ በሚገኙ መንደሮች ውስጥ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ፈጽሟል።” ብሏል፡፡ የሱዳን ዶክተሮች ሠራተኛ ማኅበር የሟቾች ቁጥር 300 መኾኑን ሲያስታውቅ መግለጫው ቁጥሩ 433 አድርሶታል። በሲቪሎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን የሚከታተለው የአደጋ ጊዜ ጠበቆች የመብት ተሟጋች ቡድን ትላንት ማክሰኞ ማለዳ በሰጠው መግለጫ፣ “ባለፉት ሦስት ቀናት ውስጥ፣ ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ ከ200 በላይ ሰዎች በፈጥኖ ደራሽ ጥቃቶች መገደላቸውን” ጠቅሶ ሌሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ቆስለዋል ብሏል። “ጥቃቶቹ ግድያ፣ አፈና፣ በግዳጅ መሰወር፣ ዝርፊያ እና ለማምለጥ የሚሞክሩት ላይ ጥይት መተኮስ ይገኙበታል” ሲል ቡድኑ ገልጿል። የባህል እና ማስታወቂያ ሚኒስትር ካሊድ ዓሊ አሌይሲር ፌስቡክ ላይ እንደተናገሩት፣ በነጭ አባይ ግዛት ውስጥ፣ በአልቃዳሪስ እና በአል ኻልዋት መንደሮች የተፈጸሙት የቅርብ ጊዜዎቹ የፈጥኖ ደራሽ ጥቃቶች "መከላከያ በሌላቸው ሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸሙ ስልታዊ ጥቃቶች ናቸው”ብሏል።
👍 ❤️ 😂 🙏 😮 🥹 25

Comments