
VOA Amharic
February 24, 2025 at 04:11 PM
🎙 ዜና እፍታ
- በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ "አነገሽ" በተባለው ቀበሌ “ሐሙስ ገበያ” በተባለች ቦታ ሐሙስ የካቲት 13/2017 ዓ.ም. ገበያ ዳር በሚገኙ ተያይዘው በተሠሩ ንግድ ቤቶች ላይ ተፈጸመ በተባለ የድሮን ጥቃት ሰዎች መሞታቸውንና መቁሰላቸውን የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የሟች ቤተሰቦች እና የዓይን እማኞች ተናግረዋል።
- የሶማሊያ እና የኢትዮጵያ የጸጥታ ባለሥልጣናት በአዲሱ የአፍሪካ ኅብረት ተልዕኮ ውስጥ የኢትዮጵያን ወታደሮች ተሳትፎ የሚያረጋግጥ ስምምነት ተፈራረሙ።
- በሳምባቸው የተፈጠረ ኢንፌክሽን በኩላሊታቸው ላይ ጉዳት ማድረሱን ተከትሎ ላለፉት ዐሥር ቀናት በሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው የቆዩት የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ በተሻለ የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ቫቲካን አስታውቃለች።
- በዩክሬን የሚካሄደውን ጦርነት ማስቆም በተመለከተ፣ በአንድ ወገን በአሜሪካ በሌላ ወገን ደግሞ በዩክሬን ተረቀው ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የቀረቡ የውሳኔ ሐሳቦች ዛሬ ሰኞ ድምፅ እንደሚሰጥቸው ይጠበቃል።
- የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ በዩክሬን ያለውን ጦርነት ማቆም እንደሚያስፈልግ በድጋሚ ሲያሳስቡ፣ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ ለሰላም ሲባል ስልጣን ለመልቀቅ ፈቃደኛ እንደሚሆኑ ተናግረዋል ። ዛሬ ሰኞ ሩሲያ ዩክሬንን የወረረችበት ሦስተኛ ዓመት ይታሰባል፡፡
👉 ተጨማሪ ዘገባዎችን በመደበኛ የዜና ዕወጃ ሰዓታችን ያገኛሉ፡፡
👍
❤️
😂
14