VOA Amharic

VOA Amharic

12.6K subscribers

Verified Channel
VOA Amharic
VOA Amharic
February 25, 2025 at 03:34 PM
ሰሜን ምዕራብ ኮንጎ ውስጥ የተከሰተ ያልታወቀ ወረርሽኝ ከ50 በላይ ሰዎችን መግደሉን ከሥፍራው የሚገኙ ሃኪሞች እና የዓለም ጤና ድርጅት ባለሥልጣናት በትላንትናው ዕለት አስታውቀዋል። https://amharic.voanews.com/a/unknown-illness-kills-over-50-in-part-of-congo-with-hours-between-symptoms-and-death/7987398.html የመጀመሪያው የበሽታው ምልክቶች በሚታዩበት እና ለሕመሙ የታጋለጠ ሰው ለሕልፈት በሚዳረግበት መካከል ያለው ጊዜ በአማካይ የ48 ሰዓታት ዕድሜ ብቻ መሆኑን ጠቅሰው፣ “በእጅጉ አሳሳቢ ያደረገውም ይህ ሁኔታ ነው” ሲሉ የክልሉ የወረርሽኞች መከታተያ ማእከል የሆነው የቢኮሮ ሆስፒታል የሕክምና ድሬክተር ሰርጅ ንጋሌባቶ ወረርሽኙን አስመልክቶ ለአሶሺየትድ ፕሬስ በሰጡት አስተያየት አስረድተዋል። ባለፈው ጥር 23 ቀን 2017 ዓም የተቀሰቀሰው ወረርሽኝ ለሕልፈት የተዳረጉትን 53 ሰዎች ጨምሮ እስካሁን 419 ሰዎች ለበሽታው መጋለጣቸው ተዘግቧል። የዓለሙ ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቢሮ አክሎ እንዳመለከተው የበሽታው መከሰት የታወቀው የመጀመሪያዎቹ የወረርሽኙ ሰለባ የሆኑ ሶስት ህጻናት፣ የሌሊት ወፍ ሥጋ ከተመገቡ እና በ48 ሰዓታት ዕድሜ ከፍተኛ ትኩሳትና የደም የመፍሰስ አደጋ የሚያስከትሉ በሽታዎች ምልክቶችን አሳይተው ለሕልፈት ከተዳረጉ በኋላ ነው።
👍 😂 5

Comments