VOA Amharic 
                                
                                    
                                        
                                    
                                
                            
                            
                    
                                
                                
                                February 26, 2025 at 05:25 PM
                               
                            
                        
                            📷:ዩክሬን፣ ኪቭ ውስጥ የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት በደረሰበት ቦታ የእሳት አደጋ ሠራተኞች በሥራ ላይ፣ የካቲት 19 ቀን 2017 ዓ.ም.
👉   በኪቭ እና ዶኔትስክ ክልሎች ቢያንስ ሰባት ሰዎች በሩስያ የአየር ጥቃት መገደላቸውን የዩክሬን ባለሥልጣናት ዛሬ አስታውቀዋል፡፡
የዶኔትስክ አስተዳዳሪ ቫዲም ፊላሽኪን በቴሌግራም ባስተላለፉት መልዕክት እንዳስታወቁት የሩስያ ኅይሎች  ኮስትያንቲኒቭካ ከተማን ለማጥቃት 'ጋይድድ ቦምብ' የሚባሉትን የተወሰነ ዒላማ ላይ ተነጣጥረው የሚተኮሱ ፈንጂዎችን ተጠቅመዋል፡፡ 
በዚህም ቢያንስ አምስት ሰዎች መገደላቸውንና ስምንት መቁሰላቸውን የመጀመሪያ ደረጃ መረጃው እንደሚያሳይ ገልጸዋል። የኪቭ ክልል አገረ ገዥ  ማይኮላ ካላሽኒክ በበኩላቸው  የሩስያ ጥቃቶች ቢያንስ ሁለት ሰዎችን  የገደሉ ሲሆን ሌሎች ሁለት ደግሞ ቆስለዋል ብለዋል።
                        
                    
                    
                    
                        
                        
                                    
                                        
                                            🥺
                                        
                                    
                                    
                                        1