
VOA Amharic
February 26, 2025 at 05:29 PM
ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ወደ አሜሪካ መጥተው የሥራ ዕድልን መፍጠር ለሚሹ የውጪ ባለሃብቶች ለመኖሪያ ፈቃድ የሚያገለግላቸውን እና ‘ጎልድ ካርድ’ ብለው የሰየሙትን በ5 ሚሊዮን ዶላር መሸጥ እንደሚሹ አስታውቀዋል።
https://amharic.voanews.com/a/us-trump-gold-cards/7988995.html
በሁለት ሳምንታት ውስጥ እንዲጀምር በሚሹት የስደተኞች ፕሮግራም የሚሸጠው ‘ጎልድ ካርድ’ በቀጥታ የግሪን ካርድ ባለቤት እንደሚያደርግና ዜግነት ለማግኘት የሚደረግው ሂደት አካል እንደሚሆን አስታውቀዋል።
‘ጎልድ ካርድ’ ያላቸው ባለሀብቶች በአሜሪካ ለመሥራት፣ የሥራ ዕድልን ለመፍጠር ኩባንያዎችን ለመመስረትና እንዲችሉ እንዲሁም ታክስም እንደሚከፍሉ አስታውቀዋል።
👍
❤️
😂
😢
🥺
10