VOA Amharic

VOA Amharic

12.6K subscribers

Verified Channel
VOA Amharic
VOA Amharic
February 26, 2025 at 07:13 PM
ሰሞኑን በአዲሰ አበባ ከተማ ለአራት ቀናት የቆየ ውይይት ያካሄዱት ተቃዋሚዎቹ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሁሉን አካታች የኦሮሚያ ክልል የሽግግር መንግሥት እንዲመሰረት እንደሚሠሩ ገልጸዋል። “ሐሳቡ የቀረበው ምርጫ ከመካሄዱ በፊት ሰላም ለማምጣት የጋራ መንግሥት ስለ ሚያሰፈልግ ነው” ሲሉ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር መረራ ጉዲና ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል። https://amharic.voanews.com/a/ofc-and-olf-call-for-transitional-government/7989095.html “የኢትዮጵያ መንግሥት በሕገ መንግሥቱ መሠረት በምርጫ የተቋቋመ ነው” ያሉት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ቃል አቀባይ ኃይሉ አዱኛ በበኩላቸው፣ የፓርቲዎቹ መግለጫ ኢ-ሕገ መንግሥታዊ ነው” ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ምላሽ ሰጥተዋል።
👍 ❤️ 😮 😂 🙏 16

Comments