VOA Amharic
February 27, 2025 at 07:00 PM
በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ወረዳ፣ ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ በደረሰ የመኪና አደጋ የ16 ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ የሰሜን ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡
የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ትምህርት እና ሥልጠና ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር ይበልጣል መርሻ፣ ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ በስልክ እንደገለጹት፣ በዕለቱ ተሽከርካሪው፥ ከበየዳ ወደ ደባርቅ ወረዳ ሰዎችንና እህል ጭኖ በመጓዝ ላይ እያለ፣ ከረፋዱ 3፡30 ገደማ፣ ልዩ ስሙ “አበርጊና” በተባለ ቦታ ላይ ተገልብጦ 16 ተሳፋሪዎች ሲሞቱ፣ በ35ቱ ላይ ቀላል እና ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሷል።
በዐማራ ክልል የሰሜን ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ትምህርት እና ሥልጠና ክፍል ሓላፊ ኢንስፔክተር ይበልጣል መርሻ፣ ዛሬ ኀሙስ ለአሜሪካ ድምፅ በስልክ እንደገለጹት፣ ከትላንት በስቲያ የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም. ከረፋዱ 3:30 ገደማ፣ የሰሌዳ ቁጥሩ ኢት-11591 የኾነ፣ በተለምዶ ካሶኒ እየተባለ የሚጠራ የደረቅ ጭነት መኪና፣ ከበየዳ ወደ ደባርቅ ከተማ እየተጓዘ ሳለ፣ ልዩ ስሙ አበጊና በተባለው ስፍራ ላይ በመገልበጡ በተሳፋሪዎች ላይ የምት እና የመቁሰል አደጋ መድረሱን ተናግረዋል።
ከ16ቱ ሟቾች መካከል አራቱ ተፈናቃዮች ናቸው፤ ያሉት ኢንስፔክተር ይበልጣል፣ የጭነት መኪናው አሽከርካሪ እስከ አኹን በቁጥጥር ሥር እንዳልዋለ ተናግረዋል። ✔️ ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3EZjodE
👍
❤️
6