VOA Amharic
February 27, 2025 at 07:35 PM
በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ምሥራቃዊ ክፍል የአማጺው ኤም 23 መሪዎችና ነዋሪዎች ሰልፍ ማድረጋቸውን ተከትሎ በተከሰተ ፍንዳታ 11 ሰዎች ሲሞቱ 65 የሚሆኑ ተጎድተዋል።
በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች የተጋሩ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች በርካታ ሰዎች ሲሸሹ እና በደም የተለወሱ አስከሬኖችም መንገድ ላይ ወድቀው አሳይተዋል።
https://amharic.voanews.com/a/congo-explosion/7990590.html
ፍንዳታዎቹ በተከሰቱበት ወቅት የኤም 23 መሪዎች በማዕከላዊ ቡካቩ ከተማ ከነዋሪዎች ጋራ ውይይት በማድረግ ላይ ነበሩ።
👍
❤️
😂
😢
12