
Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
January 30, 2025 at 06:34 PM
‹‹የክህሎት ኢትዮጵያ›› ተሳታፊዎች የፈጠራ ሀሳባቸውንና ቴክኖሎጂዎቻቸውን ከተለያዩ ተቋማት ለተገኙ ባለሙያዎች የሚያቀርቡበት መርሃ ግብር ተጀምሯል።
መርሐግብሩን ያስጀመሩት የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር ባስተላለፉት መልዕክት፣ በሀገራችን ብዙ አዳዲስ ነገር መፍጠር የሚችሉ ዜጎች በመኖራቸው በቁጭት የተጀመረ ነው።
በመጀመሪያው የቴክኖሎጂና የፈጠራ ሀሳብ ማበልፀጊያ መርሃ ግብር የተሳተፉ ወጣቶች ሥራዎቻቸውን ወደ ሙሉ ምርት የማሸጋገር ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል።
‹‹በአገራችን የክህሎት ልማት ሥራ ብዙ የተደከመበትም ቢሆንም የቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ ፕሮግራሞችን እስከጀመርንበት እስካለፈው ዓመት ድረስ ተገቢውን ቅርጽ አልያዘም ነበር ብለዋል፡፡
የኢኒስቲትዩቱ የቴክኖሎጂ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፀዳለ ተክሉ በበኩላቸው፣ የውድድሩ ተሳታፊዎች አስቀድሞ የልል ክህሎት(soft skill) ስልጠና እንደተሰጣቸው አመላክተዋል።
አሁን በተጀመረው መርሃ ግብር ሀሳባቸውን በአግባቡ በመሸጥ ውጤታማ ሆነው የሚያልፉ ተሳታፊዎች በቀጣይ ክህሎታቸውን የሚያሳድጉ የተለያዩ የሙያ ስልጠናዎችን አንዲወስዱ በማገዝ ወደ ምርት እስኪሸጋገሩ የተለያዩ ድጋፎች እንደሚደረግላቸው ገልፀዋል።
በመርሃ ግብሩ ከሁሉም የሀገሪቱ የተወጣጡ 147 የሚሆኑ አዳዲስ የፈጠራ ሀሳብና ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂ ይዘው የቀረቡ ተሳታፊዎች ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ ተመላክቷል።
መርሃ ግብር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩቱ እና የኢንተርኘሪነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ጋራ በትብብር የሚዘጋጅ ነው።
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥር 22፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/
👍
2