Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia WhatsApp Channel

Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia

4.8K subscribers

About Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia

Welcome to the official whatsApp channel of the Ministry of Labor & Skills - Ethiopia. The channel is used to provide information and updates related to skills development, job creation, and other labor-related matters in the country.

Similar Channels

Swipe to see more

Posts

Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
6/17/2025, 9:21:39 AM

⚠️ለጥንቃቄ ⚠️ ✅ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለዜጎች ምቹ፣ ዘላቂና ጥራት ያለው የሥራ ዕድል ለመፍጠር በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡ በዚህም በሀገር ውስጥ፣ በውጭ ሀገር እና በርቀት የሥራ ዕድሎች ያሉ አማራጮችን ሁሉ አሟጦ ለመጠቀም ሰፊ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ ተጨባጭና ተስፋ ሰጪ ውጤቶችም ተገኝተውበታል፡፡ 🚨ከአሳሳች ማስታወቂያዎች ራስዎን ይጠብቁ❗️ ✅ህገወጦች 🇨🇦ካናዳና 🇪🇺አውሮፓን ጨምሮ የሁለትዮሽ ስምምነት ወዳልተገባባቸው ሀገራት እንልካለን የሚሉ አሳሳች ማስታወቂያዎችን እያሰራጩ ይገኛል፡፡ ይህም ዜጎችንን ላልተገባ እንግልትና ወጪ እንዲሁም ለህገወጥ የሰዎች ዝውውር የሚዳርግና ህይወትዎን ለከፋ አደጋ የሚያጋልጥ ነው፡፡ ✅እርስዎም በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ለመሆን ፍላጎቱ ካልዎት ላላስፈላጊ ወጪና እንግልት እንዲሁም ለከፋ አደጋ ከሚዳርግዎ ህገ-ወጥ ዝውውር እራስዎን እንዲጠብቁ እየገለጽን የሚከተሉትን መረጃዎች ልብ እንዲሉ እናሳስባለን! 🌍 የሁለትዮሽ ስምምነት የተገባባቸው ሀገራት የትኞቹ ናቸው ❓ ✅ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በአሁን ወቅት ህጋዊ የሥራ ስምሪት እየሰጠባቸው የሚገኙ ሀገራት የሚከተሉት ሀገራት ናቸው፡- 1️⃣ሳዑዲ አረቢያ🇸🇦 2️⃣የተባበሩት አረብ ኤሚሬት🇦🇪 3️⃣ሊባኖስ🇱🇧 4️⃣ኳታር🇶🇦 እና 5️⃣ኩዌት🇰🇼 ናቸው፡፡ 📢ልብ ይበሉ❗️ ❌ ከላይ ከተጠቀሱት ሀገራት ውጪ ህጋዊ የሥራ ስምሪት የሚሰጥባቸው ሀገራት የሉም፡፡ ✍️ህጋዊ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ለመሆን👇 📚 የውጭ ሀገር ሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን የሚፈልግ ማንኛውም ሰው የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ (lmis.gov.et) በመጠቀም የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ በመመዝገብ ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ መሆን ይችላል፡፡ 📚ከዚህ ባለፈ ወቅታዊና በቂ መረጃ ይኑርዎ! ለዚህም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ይፋዊ ድረ-ገጽን፣ የማህበራዊ ትስስር ገጽን፣ የብሔራዊ መገናኛ ብዙሃንን እና ተዓማኒነት ያላቸው ሌሎች የመገናኛ ብዙሃን ተቋማትን እንደ መረጃ ምንጭነት ይጠቀሙ፡፡ አልያም አቅራቢያዎ በሚገኙ የክልል፣ የከተማ አስተዳደርና በየደረጃው ያሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መዋቅሮች በመገኘት መረጃ ማግኘት ይችላሉ! 🛑 አጠራጣሪ ነገር ሲያጋጥሞ በአቅራቢያዎ ለሚገኝ የህግ አስከባሪ አካላትና በየደረጃው ለሚገኝ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መዋቅር ያሳውቁ❗️ 📢 ይህን መልዕክት ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ♻️ ✅ ሌሎችም ላላስፈላጊ ወጪና እንግልት እንዳይጋለጡ ያድርጉ❗️ ሰኔ 10፤ 2017 ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ በሚከተሉት የማህበራዊ ትስስር ገፆች ይከታተሉን፡ በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y ቲክቶክ:- tiktok.com

Post image
Image
Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
6/17/2025, 12:00:01 PM

ተጠናክሮ የቀጠለው የ5 ሚሊየን ኮደርስ ስልጠና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት  የኮዲንግ ስልጠና በትኩረት እየሰጡ ይገኛል፡፡ በዚህም በርካታ ዜጎች አለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፍኬት ባለቤት መሆን ችለዋል፡፡ የኮዲንግ ስልጠናው በትኩረት እየተሰጠ ከሚገኝባቸው ክልሎች አንዱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ይገኝበታል፡፡ በአሁን ወቅት 4 ሺህ የሚጠጉ ዜጎች በክልሉ በሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የኮዲንግ ስልጠና እየወሰዱ ይገኛል፡፡ ከነዚህ መካከል በርካታዎች ስልጠናቸውን አጠናቀው የሰርተፍኬት ባለቤት መሆን ችለዋል፡፡ በክልሉ የኮዲንግ ስልጠና በትኩረት በመስጠት ጥሩ አፈጻጸም እያስመዘገቡ ከሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መካከል የወራቤ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ተጠቃሽ ነው፡፡ ኮሌጁ የኢትዮ ኮደርስ  ስልጠና አፈፃፁሙን በአሁን ወቅት 94 በመቶ ማድረሱን የኮሌጁ ዲን አቶ ቡላድ ናሙዝ ገልፀዋል፡፡ ኮሌጁ በቅድሚያ አሰልጣኝ መምህራን የኮዲንግ ስልጠናውን እንዲወስዱ በማድረግ  የሰርተፍኬት ባለቤት እንዲሆን ያደረገ ሲሆን 593 ሰልጣኞች  ስልጠናውን በማጠናቀቅ የሰርተፍኬት ባለቤት እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ  ከታቀደው 740 የኢትዮኮደርስ  ሰልጣኞች እስከ ግንቦት 30/2017 ድረስ 696 ሰልጣኞች የሰርተፍኬት ባለቤት እንዲሆኑ በማድረግ የኮሌጁን የኢትዮ ኮደርስ አፈፃፀም 94% ማሳካት መቻሉን ከክልሉ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ ሰኔ 10፤ 2017 ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ በሚከተሉት የማህበራዊ ትስስር ገፆች ይከታተሉን፡ በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y ቲክቶክ:- tiktok.com

Post image
Image
Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
6/11/2025, 9:41:35 AM

ለውጭ ሀገር የሥራ ፈቃድ አገልግሎት ፈላጊዎች በሙሉ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የውጭ ሀገር ዜጎች አዲስ የሥራ ፈቃድ ፣ የእድሳት፣ የክሊራንስና የጠፋና የተበላሸ ሥራ ፈቃድ ምትክ አገልግሎት በሥራ ገበያ መረጃ ድረገፅ www.lmis.gov.et አማካኝነት በቀጥታ እየሰጠ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ አሁን ደግሞ ተጠቃሚዎች የአገልግሎት ክፍያቸውን በቴሌብር አማካኝነት መፈፀም፣ የሚላክላቸውን IMV ቁጥር ተጠቅመው የሥራ ፈቃዳቸውን በድረ ገፁ ላይ ማግኘትና ወደ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መ/ቤት መምጣት ሳይጠበቅባቸው አትመው መጠቀም የሚችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አገልግሎቱን በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በኩል ማግኘት እንደሚችሉም ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር For All Foreign Work Permit Applicants The Ministry of Labor and Skills now provides all foreign work permit services—including new applications, renewals, clearances, and replacements—online via www.lmis.gov.et. Applicants can pay service fees through Telebirr, use the provided IMV number, and print their permits directly from the website—eliminating the need to visit the Ministry in person. Services are also available at the Mesob One-Stop Service Center. Ministry of Labor and Skills

Post image
💞 2
Image
Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
6/7/2025, 5:36:13 AM

የደቡብ ኢትዮጵያ ለኮሌጅ አመራሮችና አሰልጣኝ መምህራን የብቃት ማረጋገጫ ምዘና ጀመረ። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ለኮሌጅ አመራሮችና አሰልጣኝ መምህራን የብቃት ማረጋገጫ ምዘና መስጠት ጀምሯለሰ። የቢሮ ኃላፊ እቶ አብዮት ደምሴ በአርባ ምንጭ ክላስተር የብቃት ማረጋገጫ ምዘና ማስጀመሪያ መድረክ ላይ ምዘናው በክልሉ በሰባቱ ክላስተሮች የሚከናወን ሆኖ በአርባ ምንጭና በቦዲቲ ክላስተር ምዘና ሂደቱ መጀመሩን አሳውቀዋል። የብቃት ማረጋገጫ  ዓላማ በራሱ የሚተማመን ብቃት ያለው ዜጋ መፍጠር ፣  የክህሎትና የዕውቀት ክፍተትን በመለየት ማሟያ ግብዓት ዝግጅት በማድረግ ብቁና ተወዳዳሪ አሰልጣኝ ማፍራት መሆኑ ተገልጿል፡፡ የአሰልጣኝ መምህራን የክህሎት ክፍተት ማሟያ ስልጠና በ2016 ዓ/ም ክረምት መሰጠቱን ጠቅሰው በ2017 ዓ/ም ክረምትም የክህሎትና የዕውቀት ክፍተት በምዘና ከተለየ በኋላ ክፍተቱን መሰረት በማድረግ ምዘናው የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል። ግንቦት 30፤ 2017 ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ በሚከተሉት የማህበራዊ ትስስር ገፆች ይከታተሉን፡ በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y ቲክቶክ:- tiktok.com

👍 2
Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
5/30/2025, 9:43:16 AM

የደብረብርሃን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የISO 9001 የጥራት የሥራ አመራር ሥርዓት ሰርቲፊኬት አገኘ ኮሌጁ ከኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የISO 9001 የጥራት የሥራ አመራር ሥርዓት ሰርቲፊኬቱን ተረክቧል። የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ኮሌጁ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት የዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን ማሟላቱን በተከናወነለት የኦዲት ሂደት ተገምግሞ ብቁ ሆኖ በመገኘቱ ሰርቲፊኬቱን እንዳገኘ አመላክቷል። በርክክብ ስነ ስርዓቱ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢ/ር መዓዛ አበራ የእንኳን ደስአላችሁ መልእክት አስተላልፈው መንግስት ለጥራት ልዩ ትክረት በመስጠት ዘመናዊ የጥራት መንደር በመገንባትና አስፈላጊ የጥራት መገልገያ መሳርያዎችን በማሟላት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎት እየሰጠ  መሆኑን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ግንቦት 22፤ 2017 ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ በሚከተሉት የማህበራዊ ትስስር ገፆች ይከታተሉን፡ በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y ቲክቶክ:- tiktok.com

Post image
Image
Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
6/5/2025, 7:32:51 PM
Post image
👍 ❤️ 9
Image
Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
5/27/2025, 4:14:59 AM

የወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራና የሌማት ትሩፋት ስራ ከቁጥር ባለፈ ትርጉም ባለው መንገድ የዜጎችን ህይወት ሊቀይር እንደሚገባ ተገለፀ። የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የ75 ቀናት የስራ ዕድል ፈጠራና የሌማት ትሩፉትና የንቅናቄ ስራዎች አፈፃፀም እንዲሁም ከስኬት ባንክ ጋር በመቀናጀት በባንኩ ዲስትሪክቶችና ቅርንጫፎች የተደረገ ኦዲት ሪፓርት በመገምገም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጧል። በግምገማ መድረኩ በዘጠና ቀናት የንቅናቄ ዕቅዱ በ35ኛው ቀን የግምገማ መድረክ የተቀመጡ አቅጣጫዎች አፈፃፀምን ጨምሮ በ75 ቀናቱ በስራ ዕድል ፈጠራና የሌማት ትሩፉት ስራዎች የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት አፈፃፀም ቀርቧል። ባለፉት 75 ቀናት በስራ ዕድል ፈጠራና የሌማት ትሩፉት ንቅናቄ ስራ በተከናወኑ ተግባራት በበጀት ዓመቱ ለመፍጠር ከታቀደው 300ሺ የስራ ዕድል ፈጠራ በ10 ወራት ከ15 ቀናት ውስጥ ብቻ 324ሺ282 ቋሚ የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉ የተገለፀ ሲሆን በዚህም ከዕቅድ በላይ መፈፀም መቻሉ ተገልጿል። ነባርና አዲስ ኢንተርፕራይዞችን በኢትዮጵያ የስራ ገበያ መረጃ ስርአት E-LMIS ከመመዝገብ አንፃር 13ሺ15 ኢንተርፕራይዞች ማደራጀት መቻሉንና አሁንም ከውጤታማነት አንፃር ክፍተት መኖሩ ተገልጿል። በሌማት ትሩፋት 2ኛ ዙር ንቅናቄ መርሀ ግብር አምስት ግቦች ተጥለው ወደ ተግባር መገባቱ የተገለፀ ሲሆን በዘርፉ ለ9ሺ528 ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠሩ ተመላክቷል። በንቅናቄ በተሰራው ስራ የግብአት አቅርቦት ችግር ለመፍታት ጥረት መደረጉንና የከተማ ግብርና ስራ ባህል እየሆነ መጥቷል ተብሏል ነገር ግን ወቅታዊ የኑሮ ውድነትና የገበያ ዋጋ ከማረጋጋት አንፃር አሁንም በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል። የግምገማ መድረኩ ሌላኛው የትኩረት ነጥብ ከብድር አቅርቦት ጋር በተያያዘ ስኬት ባንክ እያደረገ ያለው የፋይናንስ አቅርቦት እንዲሁም ብድር ለመስጠት የባንኩ ቅድመ ሁኔታዎች ምን ይመስላሉ የሚለውን በመዳሰስ ከብድር ፈላጊዎች ጋር በተያያዘ አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ አሟልቶ አለመቅረብ አንዱ ተግዳሮት መሆኑ ተገልጿል። የውይይት መድረኩን የመሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ የወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራና የሌማት ትሩፋት ስራ ከቁጥር ባለፈ ትርጉም ባለው መንገድ የዜጎችን ህይወት ሊቀይር ይገባል ብለዋል። አቶ ጥራቱ አያይዘውም በየጊዜው በተካሄዱ የግምገማ መድረኮች በክፍለ ከተሞች መካከል የፉክክር መንፈስ በመፍጠር በአፈፃፀም ዝቅተኛ የነበሩ ጽሕፈት ቤቶች ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ አስችሏል ሲሉ ተናግረዋል። የሌማት ትሩፋት ስራውን ከሌሎች ተግባራት ጋር አቀናጅቶ በምራት የኑሮ ውድነቱን በማረጋጋት ያለውን አስተዋፅኦ በመረዳት በትኩረት መሰራት እንዳለበትም በመድረኩ ተጠቁሟል። የግምገማ መድረኮቹ ዓላማ የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መሆኑን በመረዳት በቀሪ የበጀት ዓመቱ ጊዜያት ዕቅዱን ለማሳካት ርብርብ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አቅጣጫ መቀመጡን ከቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ግንቦት 19፤ 2017 ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ በሚከተሉት የማህበራዊ ትስስር ገፆች ይከታተሉን፡ በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y ቲክቶክ:- tiktok.com

Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
2/7/2025, 9:43:03 AM

የ4ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተጠናቀቁ መሆኑ ተገለፀ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ በተገኙበት የቅድመ ዝግጅት ሥራው ያለበት ደረጃ ተገምግሟል፡፡ የውድድር ፓኬጁን ጨምሮ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎቹ እየተጠናቀቁ እንደሚገኝ ክብር ዶ/ር ተሻለ ገልፀዋል፡፡ በሁሉም ክልሎች ከተቋማት ጀምሮ በየደረጃው በሚካሄድ ውድድር አሸናፊ የሆኑ ሰልጣኞች፣ አሰልጣኞችና ኢንተርፕራይዞች የሚካፈሉበት ትልቅ ሀገራዊ ሁነት እንደሆነም ተመላክቷል፡፡ ውድድሩ ክህሎት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማትን ከማፋጠን አኳያ ያለውን ሚና በሚያልቅ መልኩ እንደሚካሄድም ነው የተገለፀው፡፡ 4ኛ ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር የዓለም አቀፉ የክህሎት ተቋም ኢትዮጵያን አባል ሀገር አድርጎ ከተቀበለ በኋላ የሚካሄድ የመጀመሪያው ውድድር ነው፡፡ ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡ ጥር 30፤ 2017 በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/

👍 1
Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
2/3/2025, 3:55:22 PM
Post image
Image
Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
2/8/2025, 8:10:26 AM
Post image
Image
Link copied to clipboard!