Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
February 5, 2025 at 12:17 PM
ኢ- ለርኒግ ……..የዜጎችን ብቃትና ተወዳዳሪነት ለማጎልበት የሚያስችል የሥልጠና ስርዓት በመላው ሀገራችን ያለውን ሠሪ ኃይል ምርታማነትና ውጤታማነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥርዓትን መዘርጋት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተቋቋመበት ዓላማዎች መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ይህን ተልዕኮውን በብቃት ለመወጣት የሰው ሰራሽ አስተውሎትን መሰረት ባደረገ ቴክኖሎጂ የሚታገዝ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓትን በራሱ አቅም አልምቶ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ካሉት ከ23 በላይ አገልግሎቶች መካከል አንዱ የሆነው ኢ-ለርኒግ ስርዓት ዜጎች ባሉበት ቦታ ሆነው በሥራ ገበያው ላይ ተወዳዳሪ የሚያደርጓቸውን ስልጠናዎችን ለመከታተል እንዲችሉ የለማ ስርዓት ነው፡፡ ሥርዓቱ የዜጎችን ብቃት ከማጎልበት አንፃር ያለውን ጉልህ ፋይዳ የሚያስተዋውቅና ለሥርዓቱ ውጤታማነት በሥነ ምህዳሩ ላይ ያሉ ባለድርሻ አካላትን ለማስተሳሰር የሚያስችል የምክክር መድረክ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አዘጋጅነት ተካሂዷል፡፡ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ፕሮጀክት(E-lmis) አስተባባሪ አቶ ብርሃኑ አለቃ የሀገራችን የሥራ ገበያ የሰው ኃይል ፍላጎትና በትምህርት ተቋማት የሚሰጡ ስልጠናዎች መካከል ከፍተኛ ክፍተት መኖሩን በፕሮጀክቱ ተሰበሰቡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱ ገልፀዋል፡፡ ይህን የአቅርቦትና ፍላጎት ክፍተት ከመሙላት አንፃርም የገበያውን የሥራ ፍላጎት የማጥናት ሥራ በሰፊው ሲሰራ መቆየቱን የገለፁት አቶ ብርሃኑ ገበያው የሚፈልገውን ብቁ ሠሪ ኃይል ከማቅረብ አንፃርም የ ኢ- ለርኒኒግ ስርዓቱ መልካም አማራጭ ሆኖ መምጣቱን አስረድተዋል፡፡ ዜጎች ይህን ሥርዓት አውቀውና ተገንዝበው ብሎም ፋይዳውን ተረድተው እንዲጠቀሙበት ለማስቻል የባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ቅንጅት በይበልጥ መጠናከር እንደሚኖርበትም መድረኩ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል፡፡ በመድረኩ ኢ- ለርኒግ በሀገራችን ያለበትን ደረጃና ተግዳሮቶቹን የሚቃኝና የመፍትሔ አቅጣጫን የሚያመላክት የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ የሆኑበት ውይይት ተካሂዷል፡፡ የኢትዮጵያ ገበያ መረጃ ስርዓት ዲጂታላይዜሽንን መሰረት ያደረገ እውቀትና ክህሎትን በመገንባት የሀገራችንን ሁሉን አቀፍ አድገት ከማረጋገጥ አንፃር ያለውን እምቅ አቅም በመገንዘብ ሁሉም ባለድርሻ ለውጤታማነቱ የየራሳቸውን አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ በአፅንኦት ተመላክቷል፡፡ ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡ ጥር 28፤ 2017 በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/
👍 2

Comments