
Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
February 7, 2025 at 09:43 AM
የ4ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተጠናቀቁ መሆኑ ተገለፀ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ በተገኙበት የቅድመ ዝግጅት ሥራው ያለበት ደረጃ ተገምግሟል፡፡
የውድድር ፓኬጁን ጨምሮ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎቹ እየተጠናቀቁ እንደሚገኝ ክብር ዶ/ር ተሻለ ገልፀዋል፡፡
በሁሉም ክልሎች ከተቋማት ጀምሮ በየደረጃው በሚካሄድ ውድድር አሸናፊ የሆኑ ሰልጣኞች፣ አሰልጣኞችና ኢንተርፕራይዞች የሚካፈሉበት ትልቅ ሀገራዊ ሁነት እንደሆነም ተመላክቷል፡፡
ውድድሩ ክህሎት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማትን ከማፋጠን አኳያ ያለውን ሚና በሚያልቅ መልኩ እንደሚካሄድም ነው የተገለፀው፡፡
4ኛ ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር የዓለም አቀፉ የክህሎት ተቋም ኢትዮጵያን አባል ሀገር አድርጎ ከተቀበለ በኋላ የሚካሄድ የመጀመሪያው ውድድር ነው፡፡
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥር 30፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/
👍
1