Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
February 11, 2025 at 06:35 AM
🌍ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት፣ ለሁለንተናዊ ተጠቃሚነት🌍 የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት የዜጎችን መብት፣ ደህንነትና ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መልኩ ተግባረዊ እየተደረገነው፡፡ በዚህም ባለፉት ሦስት ዓመታት በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ በሥራ ስምሪቱ ዙሪያ ተጨማሪ ግልጽነት ለመፍጠር፣ ዜጎች ህጋዊ ባልሆኑ አማራጮች ላልተፈለገ ወጪና እንግልት እንዳይዳረጉ ከዛሬ ጀምሮ በማህበራዊ ትስስር ገጾቻችን ተከታታይ መረጃዎችን እናጋራለን፡፡ 📌ምን ምን ጉዳዮች ተካተዋል? ✅ ቁልፍ መስፈርቶ፦ በሥራ ስምሪቱ ተጠቃሚ ለመሆን ማሟላት ስላለብዎ ጉዳዮች፣ ✅ ዋና ዋና ሂደቶች፦ ህጋዊ የሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ለመሆን መከተል ያለብዎት ሂደት፣ ✅ ስለስልጠና ማዕከላትና ክፍያ ስርዓት፦ የትኛው ስልጠናና የሥልጠና ማዕከል ክፍያ ይጠይቃል? ✅ የኤጀንሲዎች ዝርዝርና ህጋዊ ሥራ ስምሪት የሚካሄድባቸው፦ ህጋዊ ስራ ስምሪት ላይ ፍቃድ ያላቸው ኤጀንሲዎችና መዳረሻ ሀገራት፣ ✅ለሰለጠኑና በከፊል ለሰለጠኑ ባለሙያዎች ያሉ ዕድሎች፦ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ ባለሙያዎች በሥምሪቱ ያላቸው እድልና መከተል ያለባቸው ቅደም ተከተል፣ ✅ስኬታማ ታሪኮች፦ የህጋዊ ስራ ስምሪት ፋይዳዎች እና ስኬታማ ታሪኮች፣ ✅የርቀት የሥራ ዕድል፦ ካሉበት ሆነው ተጨማሪ ገቢ ማግኘት ስለሚችሉበት የርቀት ሥራዎች፣ ✅ጥያቄና መልስ፦ በሥምሪቱ ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣል፣ 📢 የእርስዎ ሚና የማይተካ ነው!📢 ✅ ይህንን መረጃ በማጋራት ዜጎቻችን በህገወጦች አማላይ ማስታወቂያ ተታለው ላልተፈለገ ወጪና እንግልት ብቻ ሳይሆን ለከፋ አደጋ እንዳይጋለጡ የበኩልዎን ይወጡ!🚨 ✅ በሥራ ስምሪቱ ላይ ማንኛውንም ጥያቄ ካልዎት ያድርሱን፣ 📟ይከታተሉን! 🎯 ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ! ለወዳጅ ለጓገኛዎ ያጋሩ! ስለ ውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ማንኛውም ጥያቄ ካለዎት ይላኩልን! 🎯 በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ለመሆን ፍላጎት ካልዎት ህጋዊና ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪትን ብቻ ይጠቀሙ፣ ሌሎችም እንዲጠቀሙ ያበረታቱ፣ እራሰዎንና ሌሎችንም ከአደጋ ይጠብቁ! #legaloverseasemployment #overseasopportunities #ህጋዊአማራጭ #ደህንነቱየተጠበቀሥራስምሪት ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡ የካቲት 4፤ 2017 በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/
❤️ 1

Comments