Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
February 13, 2025 at 07:25 PM
💡ስልጠና የስኬት መግቢያ በር💡 📌 በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት የመጠቀም ሀሳብ ካለዎት የመጀመሪያው ጉዳይ በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት (www. lmis.gov.et )ላይ መመዝብ ነው፡፡ 📌 ሁለተኛውና ሊታለፍ የማይችለው ነገር ስልጠና ነው፡፡ ልብ ይበሉ! ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ስልጠና  ወሳኝ ብቻ ሳይሆን የስኬት መግቢያ በር ነው፡፡ 📢ስልጠና ለምን? ✅  ብቃትና ተወዳዳሪነትዎን ይጨምራል፣ ✅  መብትና ግዴታዎን አውቀውና የሥነ-ልቦናም ጨምር ዝግጅት እንዲያደርጉ ያግዝዎታል፣ ✅  የሚሄዱበትን ሀገር ባህልና ቋንቋ እንዲያውቁና ከአሠሪዎ ጋር የተሻለ ግንኙነት መፍጠር ያስችልዎታል፣ ✅  ሁለንተናዊ ደህንነትዎ እንዲጠበቅ ፋይዳው የላቀ ነው፣ ✅  የወደፊትህ ህልምዎን ለማሳካት ተጨማሪ አቅም ይፈጥርልዎታል፡- በመስኩ ለ21 ቀናት የሚሰጠው ስልጠና ከሙያዊው ክህሎት ባለፈ ስለገንዘብዎ አስተዳደርና የራስ ሥራ ፈጠራ ላይ እውቀት እንዲኖርዎ የሚያደርጉና መሰል የህይወት ክህሎት ስልጠናዎችን ያገኛሉ፡፡ 🚨ልብ ይበሉ!🚨 ✅ ስልጠናውን ካጠናቀቁ በኋላ የብቃት ማረጋገጫ ምዘና ይወስዳሉ፡፡ ✅ የምዘናው ዋና ዓላማ ሰልጣኞችን ለማሳለፍና ለመጣል ሳይሆን በሚሰራው ሥራ ላይ ያሉ ክፍተቶችን አይቶ ለመሙላት ነው፡፡ ✅  ይህም ብቃትዎንና ተወዳዳሪነትዎን የሚያሳድግ ነውና በፍጹም ህገወጥ የብቃት ማረጋገጫ ለመግዛት እንዳይሞክሩ! 💡 ስልጠና = ብቃት = ስኬት 💡 ✅  ስልጠና ይውሰዱ! ብቃትዎን በምዘና ያረጋግጡ! ክፍተት ካለብዎ ክፍተትዎን ሞልተው ህልምዎን እውን ያድርጉ! ይህን መረጃ ለወዳጅ ጓደኛዎ በማጋራት #ከመሄድዎበፊትይሰልጥኑ ይበሏቸው፡፡ ✅  ህጋዊ አማራጭና ደህንቱ የተጠበቀ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪትን እውን ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ይቀላቀሉ! ✅  ራስዎን ለአደጋ ከሚያጋልጥ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ይጠብቁ!  #ከመሄድዎበፊትይሰልጥኑ #ደህንነቱየተረጋገጠየውጭሀገርሥራስምሪት #trainbeforeyougo #trainingmatters #legaloverseasemployment #overseasopportunities  #ህጋዊአማራጭ  #ደህንነቱየተጠበቀሥራስምሪት  ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡ የካቲት 6፤ 2017 በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/
Image from Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia: 💡ስልጠና የስኬት መግቢያ በር💡   📌 በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት የመጠቀም ሀሳብ ካለዎት የመጀመሪያው ጉዳይ ...
❤️ 1

Comments