Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
February 23, 2025 at 05:03 PM
በክልሉ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የተጀመሩ ሥራዎች ለአካባቢው ልማት ትልቅ እገዛ እያደረጉ ነው። ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በቴክኒክ እና ሙያ ዘርፍ የተጀመሩ ሥራዎች ለአካባቢው ልማት ትልቅ እገዛ እያደረጉ መሆኑን የኢፌዴሪ ሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ የሥራ ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና በክልሉ ገጠር ቴክኖሎጂና ዘር ብዜት ማስፋፊያ ኤጀንሲ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማትና የክኖሎጂ ሽግግር ስራዎችን ተመልክተዋል። ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በአሶሳ ከተማ ከተካሄደው የሕዝብ ኮንፈረንስ ጎን ለጎን ባደረጉት ጉብኝት ወቅት እንደገለጹት፣ መንግስት ባለፉት የለውጥ ዓመታት ትኩረት ሰጥቶ ከሠራባቸው ዘርፎች መካከል የተቋማት ግንባታ ዋነኛው ነው ብለዋል፡፡ ለተጀመረው የሀገረ-መንግስት ግንባታ መጠናከር ዘላቂነት ያላቸው ጠንካራ ተቋማትን መገንባት አስፈላጊ ነው ያሉት ክብርት ሚኒስትር፣ ይህም ዜጎችን ማዕከል ያደረገ አገልግሎት ለመስጠት ወሳኝ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና እንዲሁም በቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፉ የተቀረጹ ፖሊሲዎች መሬት ላይ መውረዳቸውን የሚያሳይ ናቸው ብለዋል፡፡ የዘርፉ ተቋማት ችግር ፈቺ ተግባራትን ማከናወን እንደሚጠበቅባቸው ጠቅሰው፣ ለአሶሳ ከተማ የኮሪደር ልማት የቴራዞን ምርት እያቀረበ የሚገኘው የአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለዚህ ትልቅ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና በክልሉ ገጠር ቴክኖሎጂና ዘር ብዜት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የተመለከቷቸው አበረታች ተግባራት ለተቋማት የሀብት ምንጭ ከመሆን አልፈው አካባቢውን ልማት ለማሳለጥ እያገዙ እንደሚገኙ መመልከታቸውን አስረድተዋል፡፡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለውን ሊለማ የሚችል ጸጋ በአግባቡ ለማበልጸግ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የቴክኒክና ሙያ ሥራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ መግለፃቸውን የክልሉ መንግስ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል። የካቲት 16፤ 2017 ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ በሚከተሉት የማህበራዊ ትስስር ገፆች ይከታተሉን፡ በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/

Comments