Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
Ministry Of Labor & Skills - Ethiopia
February 26, 2025 at 03:29 PM
በክልሉ 2ሽህ 246 የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራንና ዲኖች የሙያ ብቃት ምዘና ወስደዋል፡፡ የአማራ ክልል የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ በአማራ ክልል የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራንና ዲኖች አዲስ በተከለሰው የሙያ ደረጃና የሆልስቲካ የምዘና አሰጣጥ ስርዓት የሙያ ብቃት ምዘና መውሰዳቸው ተገለፀ፡፡ የክልሉ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ በ2017 በጀት ዓመት ሰባት ወራት ውስጥ በክልሉ የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራንና ዲኖች የሙያ ብቃት ምዘናን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል። በክልሉ 2ሽህ 246 የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራንና ዲኖች የሙያ ብቃት ምዘና መውሰዳቸውን የኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዘላለም አእምሮ ገልፀዋል፡፡ ጥራት ያለው ምርትና አገልግሎት ለማቅረብ በዕውቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት የበቃ እና ቴክኖሎጂን በአግባቡ መጠቀም የሚችል የሰው ኃይል ወሳኝ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ይህንን ለማሳካት አሰልጠኝ መምህራን እና ዲኖች ወቅቱ ከሚጠይቀው ሙያዊ ብቃት ወይም እውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት እረሳቸውን ለማዛመድ እንዲችሉ ምዘናው ተግባራዊ ተደርጓል ብለዋል፡፡ ምዘናው በክልሉ ባሉ 5 ክላስተር ማዕከላት የምዘና ማዕከልነት እውቅና በሚገኙ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆችና የቴክኒክ እና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች እንዲሁም በኢንዱስትሪ የምዘና ማዕከላት እየተከናወነ መኾኑንም ጠቁመዋል፡፡ የካቲት 19፤ 2017 ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ በሚከተሉት የማህበራዊ ትስስር ገፆች ይከታተሉን፡ በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/
👍 2

Comments