
የቡኻሪና ሙስሊም ሐዲሶች በአማርኛ
February 13, 2025 at 09:09 AM
መልካም ስራዎች!
ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿صَلاةُ الجَمِيعِ تَزِيدُ على صَلاتِهِ في بَيْتِهِ، وصَلاتِهِ في سُوقِهِ، خَمْسًا وعِشْرِينَ دَرَجَةً، فإنَّ أحَدَكُمْ إذا تَوَضَّأَ فأحْسَنَ، وأَتى المَسْجِدَ، لا يُرِيدُ إلّا الصَّلاةَ، لَمْ يَخْطُ خَطْوَةً إلّا رَفَعَهُ اللَّهُ بها دَرَجَةً، وحَطَّ عنْه خَطِيئَةً، حتّى يَدْخُلَ المَسْجِدَ، وإذا دَخَلَ المَسْجِدَ، كانَ في صَلاةٍ ما كانَتْ تَحْبِسُهُ، وتُصَلِّي - يَعْنِي عليه المَلائِكَةُ - ما دامَ في مَجْلِسِهِ الذي يُصَلِّي فِيهِ: اللَّهُمَّ اغْفِرْ له، اللَّهُمَّ ارْحَمْهُ، ما لَمْ يُحْدِثْ فِيهِ.﴾
“በህብረት የሚሰገድ ሶላት (አንድ ሰው) በቤቱ ወይም በሱቁ ከሚሰግደው በሃያ አምስት ደረጃ
ይበልጣል። አንደኛችሁ ውዱእ በሚገባ አድርጎ መስጂድ ሶላትን ብቻ ለመስገድ አስቦ ሲሄድ በእያንዳንዱ እርምጃ አላህ ደረጃውን ከፍ ያደርግለታል። ወንጀሉንም ያብስለታል መስጂድ እስኪገባ ድረስ። መስጊድ በገባ ጊዜም በሶላት ውስጥ እንዳለ ይቆጠርለታል። ሶላት (በህብረት ለመስገድ) እስከተጠባበቀ ድረስም መላእክት የአላህን ምሕረት ይጠይቁለታል በሚሰግድበት ቦታ ላይ ቆይታ እስካደረገ ድረስ። እንዲህ በማለት፦ አላህ ሆይ! ማረው! አላህ ሆይ እዘንለት! በቦታው ውዱእ እስካልፈታ ድረስ።”
📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 477
በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦
Telegeram፦ https://bit.ly/4ayf0xJ
Whatsup፦ https://bit.ly/486xnrS

❤️
3