
Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
February 1, 2025 at 12:15 PM
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ፖሊስ መምሪያ ቀሪ ስራዎች ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ርክክብ ተደረገ።
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በየበጀት ዓመቱ በዕቅድ ይዞ ከሚያከናውናቸው አዳዲስ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ግንባታዎች በተጨማሪ ይህን የባለቤትነት ስልጣንና ኃላፊነት በዓዋጅ ከመቀበሉ አስቀድሞ በሌሎች የአስተዳደሩ አስፈፃሚ ተቋማት ግንባታቸው ሲከናወኑ ቆይተው በተለያዩ ምክንያቶች ተቋርጠው የቆዩ ፕሮጀክቶችን ገምግሞ በመለየት እንዲጠናቀቁና የታለመላቸውን አገልግሎት እንዲሰጡ እያደረገ ይገኛል።
ቢሮው በዚህ አግባብ ካጠናቀቃቸው ፕሮጀክቶች መካከል የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ሕንፃ ፣ የልደታ ወረዳ 03 አስተዳደር ሕንፃ ፣ የልደታ ጤና ጣቢያ ፣ የንፋስ ስልክ ወረዳ 01 አስተዳደር ሕንፃ ፣ የንፋስ ስልክ ፖሊስ መምሪያ ፣ የኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ 14 ጤና ጣቢያ እንዲሁም የቤላ ጤና ጣቢያ ፕሮጀክቶች ይጠቀሳሉ።
ከነዚህ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነውና የግንባታ ስራው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀው የንፋስ ስልክ ፖሊስ መምሪያ ቀሪ ስራዎች ፕሮጀክትም በዛሬው ዕለት ይፋዊ ርክክብ ተደርጎለታል።
1 ቤዝመንትን ጨምሮ 8 ወለሎች ያሉት ዋናው የመምሪያው ሕንፃ እንዲሁም 1 ቤዝመንት ያለው ባለ 4 ወለል የታራሚዎች ማቆያ ሕንፃዎች የተካተቱበት ይህ ፕሮጀክት ከ188 ሚሊዮን ብር በላይ የውል መጠን ተይዞለት ልዩ ቦታው ጀሞ ሚካኤል ትራፊክ መብራት አካባቢ በ6 ሺህ ካ.ሜ. ቦታ ላይ የተገነባ ነው።
ዓለም-ዓቀፍና ሀገር-ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ድንጋጌዎችንና ስታንዳርዶችን ከግምት አስገብቶ በተገነባው በዚህ ፕሮጀክት የተለያዩ የአስተዳደር ክፍሎችን ጨምሮ የወንጀል ምርመራ ክፍሎች ፣ ካፊቴሪያ ፣ የታራሚዎች ማረፊያ ክፍሎች ፣ መሰብሰቢያ አዳራሽ ፣ የህፃናት ማቆያ.....