Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
February 5, 2025 at 01:41 PM
የሜክሲኮ ፓርኪንግና ታክሲ ተርሚናል ፕሮጀክት የአስፋልት ንጣፍ ስራ እየተፋጠነ ይገኛል። የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በኮሪዶር ልማቱ እያከናወናቸው ከሚገኙ በርካታ ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የሜክሲኮ ፓርኪንግና ታክሲ ተርሚናል በማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ ደርሷል። ሜክሲኮ ኬኬር ሕንፃ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በ9,200 ካ.ሜ. ቦታ ላይ እየተገነባ የሚገኘው ይህ ዘመናዊ ፓርኪንግ እና ታክሲ ተርሚናል በውስጡ ካፊቴሪያ ፣ ሱቆች ፣ የህዝብ መፀዳጃዎች ፣ የአስተዳደር ሕንፃ እና ምቹ የተሳፋሪ መጠበቂያ ስፍራ የሚሟሉለት ሲሆን ሲጠናቀቅም በአካባቢው የሚስተዋለውን ከፍተኛ የትራንስፖርት ፍሰት በማሳለጥ ለተገልጋዩ ቀልጣፋና የዘመነ አገልግሎት የመስጠት ዓቅም እንደሚኖረው ይጠበቃል። የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጥር 28/2017 ዓ/ም የቢሮውን ይፋዊ የማሕበራዊ ገፆች ይከታተሉ ፌስቡክ https://www.facebook.com/AddisConstruction/ ቴሌግራም https://t.me/AddisCityCon ትዊተር https://twitter.com/AddisCity ዩቲዩብ https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg ቲክቶክ https://tiktok.com/@design_and_construction1 ዋትሳፕ https://whatsapp.com/channel/0029Vani9gI0lwgzDJ1eFH1x ዌብሳይት www.addisconstructionwork.gov.et ነፃ የስልክ መስመር 9426
Image from Addis Ababa Design And Construction Works Bureau: የሜክሲኮ ፓርኪንግና ታክሲ ተርሚናል ፕሮጀክት የአስፋልት ንጣፍ ስራ እየተፋጠነ ይገኛል።   የአዲስ አበባ ዲዛይ...

Comments