Ahadu Radio And Television
February 25, 2025 at 03:12 PM
*#update
የብሔራዊ ባንክ ልዩ የውጭ ምንዛሪ ሽያጭ ጨረታ ተጠናቀቀ*
👉 አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ 135 ብር ዋጋ መሸጡ ተገልጿል
የካቲት 18/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዛሬው ዕለት ያካሄደው የ60 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ልዩ የውጭ ምንዛሪ ሽያጭ ጨረታ መጠናቀቁን አስታውቋል፡፡
በዚህ ልዩ ጨረታ ውጤት መሰረትም የአንድ የአሜሪካ ዶላር አማካይ የምንዛሪ ዋጋ 135 ነጥብ 6185 ብር መሆኑን ይፋ አደርጓል።
ጨረታው ላይ 27 ባንኮች መሳተፋቸው የተገለጸው ባንኩ፤ ይህም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተሳትፎ የታየበት መሆኑን ገልጿል።
ማዕከላዊ ባንኩ አክሎም፤ በቀጣይ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝና ከዋጋና ከውጭ ምንዛሪ መረጋጋት ጋር በሚስማማ መልኩ ተጨማሪ ጨረታዎችን እንደሚያካሂድ አስታውቋል።
ይህ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ የገንዘብ ገበያውን ለማረጋጋትና የውጭ ምንዛሪ ተገኝነትን ለማሻሻል የሚደረገው ጥረት አካል መሆኑንም አመላክቷል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
*ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!*
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ