
Ahadu Radio And Television
56 subscribers
About Ahadu Radio And Television
Ahadu Radio and Television is an Ethiopian media company that provides broadcasting services, including radio and television programming. It offers a variety of content such as news, entertainment, cultural programs, and educational shows aimed at the Ethiopian audience.
Similar Channels
Swipe to see more
Posts

*ለልማት በሚል ተማሪዎች በየወሩ 500 ብር እንዲከፍሉ መደረጉ አግባብ አደለም ሲሉ የተማሪ ወላጆች ቅሬታ አቀረቡ* የካቲት 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ጸሐይ ጮራ ትምህርት ቤት ተማሪዎች፤ ለልማት እና ለሕጻናት ማቆያ በሚል እስከ 5 መቶ ብር እየተጠየቁ መሆኑን የተማሪ ወላጆች ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡ በዚህም ተማሪዎች ትምህርታቸውን ለመከታተል ተጽእኖ እያሳደረባቸው እንደሚገኝ የገለጹት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፤ "መክፈል የማይችሉ ወላጆችና ተማሪዎች በአስገዳጅነት እንዲከፍሉ እየተደረገ ነው" ብለዋል፡፡ አክለውም "ይሰራል የሚባለው የሕጻናት ማቆያም ቢሆን ምንም አይነት ጅምር ሥራ የለም" ያሉ ሲሆን፤ ክፍያውን ያለደረሰኝ በአስገዳጅነት እንደሚያስከፍሉም አንስተዋል፡፡ ያለአግባብ ከሚፈጸመው ክፍያ በተጨማሪ "በትምህርት ቤት ውስጥ ከመጸዳጃ የሚወጣ ፍሳሽ በአግባቡ ባለመወገዱ በተማሪዎች ላይ የጤና ችግር እያስከተለ በመሆኑ፤ ጉዳዩን ትምህርት ቤቱ ትኩረት አልሰጠውም" ሲሉ ቅሬታቸውን አክለዉ ገልጸዋል፡፡ እንዲሁም ይህ ቆሻሻ በትምህርት ቤቱ ግቢ ውስጥ የሚያልፍ በመሆኑ፤ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ችግሩ እንዲወገድ የሚመለከተውን አካል ቢያነጋግሩም ምላሽ እንዳልተሰጣቸው ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡ አሐዱም ቅሬታዉን ተቀብሎ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ጸሐይ ጮራ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ታሪኩ ደሳለኝን አነጋግሯል፡፡ ርዕሰ መምህሩ በምላሻቸውም "ከፍሳሹ ጋር ተያይዞ የተነሳው ቅሬታ ከእውነት የራቀ እና ሆን ተብሎ የትምህርት ቤቱን ሥም ለማጥፋት የታሰበ ነው" ብለው፤ ከክፍያ ጋር በተያያዘ የተነሳው አቤቱታ ከወላጅ ኮሚቴ ጋር በመሆን እስከ 500 ሺሕ ብር የውስጥ ገቢ ለማድረግ ታቅዶ የተደረገ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ይህም ደግሞ የወላጅ ኮሚቴው እና የሚመለከተው አካል በጋራ በመሆን ስምምነት መደረጉን አንስተው፤ ምንም ያለደረሰኝ የፈጸመ ክፍያ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ከመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ጋርም ሆነ ከክፍያዉ ጋር በተያያዘ በትምህርት ቤቱ እየተከናወነ ያለው ተግባር "ከሕግ ውጭ ነው" ቢሉም፤ ርዕሰ መምህሩ በበኩላቸው "ውንጀላው ከእውነት የራቀ ነው" ብለዋል፡፡ አክለወሰም የሚስተካከሉ ክፍተቶች ቢኖሩም በውይይት መፍታት እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡ በአለምነው ሹሙ #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ *ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!* ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ


*የትራምፕ እና የዜለንስኪ የዋይት ሃውስ ውይይት የከረሩ ንግግሮች ተስተናግደውበት ያለምንም ስምምነት ተቋረጠ* 👉 ትራምፕ ዘለንስኪን "በሚሊየኖች ሕይወትና በ3ኛ የዓለም ጦርት ቁማር እየተጫወትክ ነው" ሲሉ ከሰዋል የካቲት 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የዩክሬኑ አቻቸው ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በትናንትናው ዕለት በዋይት ሃውስ ያደረጉት ውይይት የከረሩ የቃላት ልውውጦች ተስተናግደውበት ያለምንም ስምምነት ተቋርጧል። ዘለንስኪ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ጋር፤ "ኦቫል ኦፊስ" በተሰኘው የፕሬዝደንቱ ጽሕፈት ቤት ውስጥ በትናንትናው ዕለት የተጋጋሉ ንግግሮች የተሞላበት ውይይት አድርገዋል። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ከዶናልድ ትራምፕ ጋር አወንታዊ ውይይት በማድረግ አሜሪካ ከዩክሬን ልዩ ማዕድናት ማግኘት የሚያስችላት ስምምነት ለመፈረም፤ በዚህም "ከአሜሪካ ቀጥተኛ የደህንነት ዋስትና" የማግኘት ተስፋን ሰንቀው ነበር ወደ አሜሪካ ያቀኑት፡፡ ነገር ግን በምትኩ በሁለቱ መሪዎች መካከል የተደረገው ውይይት፤ ወደ ጦፈ ክርክር እና የቃላት ግጭት አምርቶ ምንም ስምምነት ሳይደረስበት ተቋርጧል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና ምክትላቸው ጄዲ ቫንስ ለዓመታት አሜሪካ ለዩክሬን ላደረገችው ድጋፍ 'እንዲያመሰግኑ' ዘለንስኪን የጠየቁ ሲሆን፤ ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በዓለም ሚዲያ ፊት 'ያልተለመደ አለባበስ' ለብሰው በመገኘታቸውም በመድረኩ ኮንነዋቸዋል። ፕሬዝዳንቱ ከሩሲያው ፕሬዝዳን ቭላድሚር ፑቲን ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ጠንክረው መስራት እንደሚገባቸው ደጋግመው ያሳሰቡት ትራምፕ እና ምክትላቸው፤ የዘለንስኪ ምላሽ "አክብሮት የጎደለው ነው" ሲሉም ወቅሰዋቸዋል። ዘለንስኪ "የሰላም ስምምነት ለመፈረም ዋስትና ያስፈልገናል" ያሉ ሲሆን፤ ትራምፕ በበኩላቸው "ለመደራደሪያ የሚሆን አቅም እና ሥልጣን የለህም" በማለት የፕሬዝዳንቱን ንግግር በድንገት አቋርጠዋል፡፡ ትራምፕ አክለውም "ያለህ አማራጭ ስምምነቱን መፈረም ነው ካልሆነ አሜሪካ ከዚህ ትወጣለች" ሲሉ አሳስበዋል። በውይይቱ የመጀመሪያ ጥቂት ደቂቃዎች ላይ መልካም የሚመስሉ ንግግሮች የተስተዋሉ ቢሆንም፣ ነገር ግን የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ "የሰላም መንገድ እና የብልጽግና መንገድ በዲፕሎማሲ ውስጥ እያለፈ ሊሆን ይችላል፡፡ ፕሬዚዳንት ትራምፕ የሚያደርጉት ይህንኑ ነው።" ማለታቸውን ተከትሎ፤ በኦቫል ቢሮ ውስጥ የነበረው የውይይት መንፈስ ወደ ውጥረት እና የከረረ ንግግር ማምራት ጀምሯል። በዚህ ወቅትም ዘለንስኪ ሩሲያ ሙሉ ወረራ ከመጀመሯ ከሦስት ዓመታት በፊት በፊት ባሉት ዓመታት ያደረሰችውን ጥቃት በመጥቀስ፤ እ.ኤ.አ. በ2019 ያልተሳካ የተኩስ አቁም ስምምነት መደረጉን አስታውሰዋል፡፡ ነገር ግን አሁንም "ማንም አላስቆመውም" ሲሉ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጦርነቱን አጠናክረው መቀጠላቸውን ተናግረዋል። ዘለንስኪ አክለውም "ምን አይነት ዲፕሎማሲ ነው ጄዲ የምታወራው? ምን ማለትህ ነው?" በማለት ለምክትል ፕሬዝዳንቱ ጥያቄ ሰንዝረዋል። ቫንስ ሲመልሱም "የአገራችሁን ጥፋት የሚያቆመው ዓይነት" ማለታቸውን ተከትሎ፤ ውይይቱ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ወደ ክርክር እና ውጥረት ተቀይሯል፡፡ ምክትል ፕሬዝዳንቱ አክለውም፤ ዘሌንስኪን በአሜሪካ ሚዲያ ፊት ለፊት ያሳዩት ባህሪ አክብሮት የጎደለው እና "ሙግት" የተሞላበት ነው በማለት ከሰዋል። ይህንን ተከትሎም ቫንስ በውትድርና እና በውትድርና አገልግሎት ላይ ባጋጠመው ችግሮችን አንስተው፤ ለዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡ ዜለንስኪም በምላሻቸው "በጦርነቱ ወቅት ሁሉም ሰው ችግሮች ያጋጥሟቸዋል። እርሶም ቢሆኑ፡፡ ግን ጥሩ ውቅያኖስ አለዎት እና አሁን አይሰማዎትም፣ ግን ለወደፊቱ ይሰማዎታል" ሲሉ ተናግረዋል። ይህም የዘለንስኪ አስተያየት በዜለንስኪ እና በምክትል ፕሬዝዳንቱ ብቻ ተወስኖ የነበረው ሙግት ላይ ትራምፕ እንዲሳተፉበት ያስገደደ ሲሆን፤ ይህም የትራምፕን ትልቁን የቁጣ ምላሽ ቀስቅሷል። "ምን እንደሚሰማን አትንገረን! ይህን ለመምከር ምንም አይነት አቋም የለህም" ሲሉም ዶናልድ ትራምፕ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ለዘለንስኪ አስተያየት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ "አሁን ካርዶቹ የሉህም" ሲሉ የተናገሩት ትራምፕ፤ "በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወት ላይ ቁማር ትጫወታለህ" ሲሉም ዘለንስኪን ወቅሰዋቸዋል፡፡ በዚህ ወቅት የዩክሬን መሪ ትራምፕ ከጦርነቱ አጥቂ ጋር የመገናኘትን የሞራል አደጋ ሊረዱ እንዳልቻሉ ጠቁመዋል። በውይይቱ ላይ ዘለንስኪ "ከጦርነቱ መጀመሪያ ጀምሮ ብቻችንን ነበርን እና አመስጋኞች ነን" ማለታቸውን ተከትሎም፤ ይህ ንግግር ዳግም ትራምፕን አስቆጥቷል፡፡ "ብቻህን አልነበርክም። በዚህ ደደብ ፕሬዝዳንት በኩል 350 ቢሊዮን ዶላር ሰጠንህ" ሲሉ ትራምፕ፤ የቀድሞውን የአሜሪካ ፕሬዝዳን ጆ ባይደን ማጣቀሻ አድርገዋል። ከዚያም ምክትል ፕሬዝዳንቱ ዜለንስኪ አሜሪካን አመስግነው እንደሚያውቁ የጠየቁ ሲሆን፤ ባለፈው ዓመት በአሜሪካ በተካሄደው ምርጫ ወቅትም "ለተቃዋሚዎች" ወይንም ለዴሞክራቶች ዘመቻ አድርገዋል ሲሉ ከሰዋል። ትራምፕ "አታሸንፍም ይህን እያሸነፍክ አይደለም" ሲሉም ዘለንስኪን የተናገሩ ሲሆን፤ "በእኛ ምክንያት ግን ከችግር የመውጣት በጣም ጥሩ እድል አለህ።" ብለዋል፡፡ ውይይቱ ወደተጋጋለ ንግግር መሸጋገሩን ተከትሎም "እንዲህ አይነት ውይይት ማድረግ በጣም ከባድ ነገር ይሆናል" ያሉት ትራምፕ፤ "አመለካከቶቹ መለወጥ ስላለባቸው ይህን ለማድረግ ከባድ ስምምነት ይሆናል" ብለዋል፡፡ በዚህ በክርክር እና መደማመጥ በጎደለበት የዋሽንግተን ውይይት ላይ፤ በአሜሪካ የዬክሬን አምባሳደር ኦክሳና ማርካሮቫ እጆቻቸውን ጭንቅላታቸውን በላይ ጭነው በጭቅጭቅ ውስጥ ሆነው ታይተዋል፡፡ ይህንንም ተከትሎ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት እና ትራምፕ ለታቀደለት የዜና ኮንፈረንስ ወደ መድረክ ከመውጣታቸው በፊት፤ ዘለንስኪ በመጨረሻ ዋይት ሃውስን ለቀው እንዲወጡ ተነግሯቸዋል። ዘለንስኪ ውይይቱን አቋርጠው በመኪና ከመውጣታቸው ጥቂት ቀደም ብሎም ትራምፕ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ፤ "ለሰላም ስትዘጋጁ ተመለሱ" ሲል ጽፈዋል። "ስምምነቱ ተዘርዟል" ሲሉም አስታውቀዋል። "የአሜሪካ ተሳትፎ የሚቀጥል ከሆነ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ለሰላም ዝግጁ እንደማይሆን ገንዝቤያለሁ። ምክንያቱም የኛ ተሳትፎ ለድርድር ትልቅ ጥቅም እንደሚሰጠው ያምናል" ብለዋል ትራምፕ በጽሁፋቸው። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በበኩላቸው ኤክስ በተሰኘው የማኅበራዊ ገጽ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ "አመሰግናለሁ አሜሪካ" ያሉ ሲሆን፤ " የአሜሬካ ፕሬዝደንት፣ የምክር ቤት አባላትንና የአሜሪካን ሕዝብ እናመሰግናለን። ዩክሬን ፍትሐዊ እና ዘላቂ ሰላም ትፈልጋለች፣ ያንን ለማግኘትም በሚገባ እየሠራን ነው" ሲሉ ገልጸዋል። በዚህም መሠረት በዚህ ሳምንት በሁለቱ ወገኖች መካከል ይደረጋል ተብሎ የተጠበቀው እና በብዙሃን ዘንድ ሙገሳን አግኝቶ የቆየው የማዕድን ድርድር በሁለቱ መሪዎች መካከል በተፈጠረው ከፍተኛ ውዝግብ ምክንያት ሳይፈረም ቀርቷል። በእዮብ ውብነህ #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ *ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!* ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com

*"የዓድዋ ድል በዓልና የኢትዮጵያ የጤና ስርዓት ሰፊ ቁርኝት አላቸው" ፕሮፌሰር አንዱአለም ደነቀ* የካቲት 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በዛሬው ዕለት ለ52ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 179 የሕክምና ተማሪዎችን አስመርቋል። በፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርስቲው ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አንዱአለም ደነቀለ የዓድዋ ድል በዓል እና ኢትዮጵያ የጤና ስርዓት ሰፊ ቁርኝት አላቸው ሲሉ ገልጸዋል። የዛሬ 129 ዓመት ኢትዮጵያ አንድም ዘመናዊ ሀኪም የጤና ባለሙያ ስላልነበራት ለጦርነት ሲሄዱ የተከተላቸው የሕክምና ባለሙያ እንዳልነበረ የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ ይህም ብቻ ሳይሆን በጦርነቱ ወቅትም የጦር ጉዳተኞችን የሚያክሙ ከሩሲያ ቀይ መስቀል የመጡ የሕክምና ባለሙያዎች እንደነበሩ አንስተዋል። ይህንን መነሻ በማድረግም የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሆስፒታል ዳግማዊ ሚኒሊክ ሊቋቋም መቻሉን በመግለጽ፤ "ከዛ በኋላ በርካታ የሕክምና ትምህርት ቤቶች መቋቋም በመቻላቸው ብቻ በዛሬው ዕለት በአንድ የሕክምና ትምህርት ቤት ብቻ በርካታ ሀኪሞችን ማስመረቅ ችለናል" ብለዋል። በኮሌጁ የመውጫ ፈተናን ከወሰዱ ተማሪዎች ውስጥ 94 ነጥብ 4 በመቶ ማለፋቸውን የተናገሩት ፕሮፌሰር አንዱአለም፤ የተገኘው ውጤት ትልቅ ቢሆንም ግን በቂ ነው ተብሎ እንደማይታሰብ በመግለጽ ሁሉም ማለፍ እንደነበረባቸው አንስተዋል። በመሆኑም ሁሉም ተማሪዎች እንዲያልፉና የተሻለ ውጤት እንዲያገኙ ለማድረግ በተማሪዎችና ባለሙያዎች ላይ ተጨማሪ ሥራን እንደሚጠይቅ ያሳሰቡ ሲሆን፤ "ወደፊት የሚወጣው ፈተናም እየከበደ እንጂ እየቀለለ ስለማይሄድ ሁላችንም መጠንከር አለብን" ሲሉ ተናግረዋል። በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ "አድዋ ሀገራችንን ሊወር የመጣውን ጠላት ድል ያደረግንበት ጊዜ ነው" ብለዋል። ይህ ምርቃት ተማሪዎች እውቀት የጨረሱበት ሳይሆን ከወጡ በኋላም ነገ በተግባር የሥራ ባህልን የሚያሳድሩበትና የኅብረተሰቡን ባህል በመረዳት በቅንነት ማስተናገድ እንደሚገባቸው በመጥቀስ፤ "ሕሙማኑን ከልባችሁ ለማገልገል የገባችሁትን ቃለመሃላ ሁሌም ልታስቡት ይገባል" ብለዋል። በኢትዮጵያ የሚሰጠውን የሕክምና አገልግሎትም ወደላቀ ደረጃ ያሳድጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል። የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ በበኩላቸው፤ ለተመራቂ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ተማሪዎች ወደሥራ ዓለም ሲሰማሩ ሕዝባቸውን በቅንነትና በታማኝነት ማገልገል እንደሚገባቸው አሳስበዋል። በምርቃት ሥነ-ስርዓቱ ላይም በዘንድሮው ዓመት በአዲስ አበባ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከፍተኛውን ውጤት ያመጣችው ተመራቂ ኤልሳቤጥ አርአያ የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ ሆናለች። በስፍራሽ ደመላሽ #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ *ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!* ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

*የሸገር ከተማ አስተዳደር ከገላን እስከ ዲማ የሚደርስ የባቡር መስመር ለመዘርጋት ማቀዱን አስታወቀ* የካቲት 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሸገር ከተማ አስተዳደር ከገላን እስከ ዲማ የሚደርስ የባቡር መስመር ለመዘርጋት የሚያስችል ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል። ይህ የተባለው የሸገር ከተማ አስተዳደር ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በዛሬው ዕለት ባካሄደው ውይይት ላይ ነው። ሁለት ዓመት የሞላው እና 160 ሺሕ ካሬ ስፋት ላይ ያረፈው ሸገር ከተማ አምስት ከተሞችን በማዋሀድ የተፈጠረ ከተማ ነው። በከተማው ኢንቨስትመንትን ለመሳብ በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ የገለጹት የሸገር ከተማ አሰሰተዳደር ከንቲባ ተሻለ አዱኛ (ዶ/ር)፤ ይህንን ተከትሎም ከሰሞኑ ከባለሀብቶች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ተናግረዋል። ከንቲባው አክለውም፤ የዚህ ቀጣይ ውይይት በዛሬው ዕለት ከባንክ እና ፋይናንስ ተቋማት ጋር መደረጉን ገልጸዋል። ከንቲባው "ሸገር ከተማ የኢኮኖሚ ከተማ ነው" ያሉም ሲሆን፤ በቀጣይ በርካታ የልማት ሥራዎች እንደሚሰሩ አብራርተዋል። በዚህም ከተማ አስተዳደሩ የባቡር መስመር የመዘርጋት ፍላጎት እንዳለው በመግለጽ፤ "ይህም ከገላን እስከ ዲማ የሚዘረጋ ይሆናል" ብለዋል። ከተማው የኮዬ ፈጬ አካባቢን ደግሞ የንግድ ቦታ የማድረግ ሀሳብ እንዳለው የገለጹ ሲሆን፤ በርካታ ሪልስቴት የሚሰራበት ቦታም ይሆናል ብለዋል። ሌላው የገላን ከተማን በከፍተኛ ሁኔታ የኢንዱስትሪ ቦታ ለማድረግም ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛል ብለዋል። በዛሬው ውሎም የፋይናንስ ተቋማት ሸገር ከተማ በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸዉ በውይይቱ ላይ ገልጸዋል። በአቤል ደጀኔ #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ *ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!* ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

*#አሐዱ_መድረክ* "የጦርነትን አስከፊነት ከአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የበለጠ የሚረዳው ያለ አይመስለኝም" አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ከ #አሐዱ_መድረክ ጋር ያደረጉት ቆይታ! (ክፍል አንድ) *ውይይቱን ለመከታተል ከሥር ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ!👇* https://youtu.be/sWAgGs6yRds?si=46ITrmWql5L9pIlD