Ahadu Radio And Television
Ahadu Radio And Television
February 26, 2025 at 09:35 AM
*ባለፉት 10 ቀናት ከመተሃራ እስከ ባቡር ትራክሽን ጣቢያ ድረስ ከፍተኛ ዝርፊያ መፈጸሙ ተነገረ* 👉 በዝርፊያው ከ6 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ መድረሱን ተገልጿል የካቲት 19/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ባለፉት አስር ቀናት ከ80 ኪሎ ሜትር በላይ የኮንዳክተር ሽቦ ገመድ እና 25 ነጥብ 7 ኪሎ ሜትር የኦ.ፒ.ጂ ደብሊው ፋይበር መስመር ለስርቆት መዳረጋቸውን፤ የአዋሽ - ወልዲያ - ሃራ ገበያ የባቡር የኃይል አቅርቦት ፕሮጀክት ቢሮ አስታውቋል። በቢሮው የሳይት ሥራ አስኪያጅ አቶ ተክለወይን ብርሃነአሰፋ እንደተናገሩት፤ ባለፉት አስር ቀናት ከመተሃራ እስከ ባቡር ትራክሽን ጣቢያ አንድ ድረስ በቡድን በተደራጀ ሁኔታ 78 ነጥብ 9 ኪሎ ሜትር የኮንዳክተር ሽቦ እና 25 ነጥብ 7 ኪሎ ሜትር የኦፕቲካል ፋይበር መስመር ዝርፊያ ተፈጽሟል። ከባቡር ትራክሽን ጣቢያ አንድ እስከ ባቡር ትራክሽን ጣቢያ ሁለት ድረስ ደግሞ፤ 2 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር የኮንዳክተር ሽቦ ገመድ በዘራፊዎች መወሰዱንም ነው የተናገሩት። በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ በዱዱብ እና ዶሆ ቀበሌዎች ሁለት ጊዜ እንዲሁም በዱለሳ ወረዳ በቡሩቱሊ እና ኢስኪለሊ ቀበሌዎች አንድ ጊዜ በተፈጸመ የስርቆት ወንጀል ሳቢያ ከ758 ሺሕ ዶላር በላይ እና በብር ከ6 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ መድረሱን ተናግረዋል። የስርቆት ወንጀሉ የተፈጸመው የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ወደ ሥራ እስኪገባ ድረስ በ33 እና 15 ኪሎ ቮልት በጊዜያዊነት ኃይል ይዞ እንዲቆይ ለማድረግ ከሥራ ተቋራጩ ጋር ምክክሮች እየተደረጉ ባሉበት ወቅት መሆኑ እንዳሳዘናቸውም ገልጸዋል። እንደ ሳይት ሥራ አስኪያጁ ገለጻ ዝርፊያ ተፈፅሞባቸው በአይሱዙ መኪና ተጭነው ሲጓዝ የነበረ የኮንዳክተር ሽቦ በአዳማ ከተማ ላይ እንዲሁም፤ በዱለሳ ወረዳ መቁረጫ ሴጌቶ ይዘው የተገኙ ሁለት ተጠርጣሪዎች ተይዘው ክስ ለመመስረት ማስረጃ እየተደራጀ እንደሚገኝ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የሳይት ሥራ አስኪያጁ አክለውም፤ በኃይል መሰረተ ልማት ስርቆት ዙሪያ ከዞን፣ ከወረዳ እና ከቀበሌ አመራሮች እንዲሁም ከፀጥታ ዘርፍ አካላት ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ ከ2 ኪሎ ሜትር በላይ የኮንዳክተር ሽቦ በዘራፊዎች መወሰዱን አብራርተዋል። በተቋሙ የኃይል መሰረተ ልማት ደህንነት፣ ክትትልና ቁጥጥር ሥራ አስኪያጅ አቶ ዋለ ታምሬ እንደተናገሩት፤ በፕሮጀክቱ ላይ የተፈጸመው የስርቆት ወንጀል እጅግ አስደንጋጭ ነው። በበጀት ዓመቱ በኦፕሬሽን ላይ የሚገኙ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ይፈጸሙ የነበሩ የስርቆት ወንጀሎች መቀነሳቸውን የገለጹት ሥራ አስኪያጁ፤ ይሁን እንጂ በግንባታ ላይ ባሉ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ስርቆቱ መቀጠሉን ተናግረዋል። #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ *ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!* ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Comments