Ahadu Radio And Television
February 27, 2025 at 10:30 AM
*35 በመቶ የሚሆኑት ደንበኞቹ በአገልግሎቱ አሰጣጡ ደስተኛ እንዳልሆኑ በጥናት ማረጋገጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለጸ*
የካቲት 20/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ደንበኞቹ ያላቸውን የእርካታ ደረጃ በተመለከተ በ3ኛ ወገን ባካሄደው ጥናት፤ ከተገልጋዮቹ መካከል 35 በመቶ የሚሆኑት በአገልግሎት አሰጣጡ ደስተኛ እንዳልሆኑ ማረጋገጡን ገልጿል፡፡
በርካታ ደንበኞች ያሉት አገልግሎቱ ጥናቱን ማካሄድ ያስፈለገው በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚታየውን ችግር ለማስተካከል እንደሆነ፤ የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ መላኩ ታዬ ለአሐዱ ገልጸዋል።
በተቋሙ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ላይ ከሚነሱ ቅሬታዎች መካከል የኃይል መቆራረጥ አንዱ መሆኑን አንስተዋል።
በተጨማሪም ተገልጋዮች ከኃይል መቆራረጥ ባሻገር ወደ ተቋሙ በመሄድ በአካል በሚስተናገዱበት ወቅት፤ በተቋሙ ሠራተኞች የደንበኛ አያያዝ ችግር እንዳለ በተደጋጋሚ ማንሳታቸው ተናግረዋል።
"በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቱ ላይ ስኬታማ ነን ለማለት አያስደፍርም" ሲሉም የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ ገልጸዋል።
የተገልጋዩን ቅሬታ ለመፍታት ያረጁ መሠረተ ልማቶችን በአዲስ የመቀየር ሥራ እየተሰራ መሆኑን በመግለጽ፤ የኃይል መቆራረጥ እንዳይከሰት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
አክለውም በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የሃይል ፍላጎት ለማሟላት እና ጥራት ያለው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለደንበኞች ለመስጠት ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በተቋሙ ሠራተኞች የደንበኛ አያያዝ ችግርን በተመለከም፤ የተለያዩ ተቋማዊና አስተዳደራዊ እርምጃዎችን በመውሰድ ችግሮችን ለመቅረፍ ሥራዎች እየተሠሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዚህም የደንበኞችን እና የባለድርሻ አካላትን የእርካታ ደረጃ ማሳደግ እንደሚገባ ተቋማዊ አቅጣጫ ተቀምጦ ወደ ተግባር መገባቱን ኃላፊው ጨምረው አስረድተዋል።
በህይወት ጌትነት
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
*ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!*
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ